እናት ለመሆን ልጅ መውለድ አያስፈልግም፡፡ እናት ለመሆን የሚጠይቀው በውስጥ ያለን የእናትነት መንፈስ ካለስስት በማውጣት ለሰዎች እንክብካቤ ማዋል ብቻ ነው፡፡
ከአመታት በፊት አንድ ታሪክ ሰማሁ፡፡ አንዲት ሴት ቃለ መጠይቅ ይደረግላት ነበር፡፡ በቃለ መጠይቁ መካከል ልጆች አለሽ ወይ ተብላ ለተጠየቀችው ጥያቄ ልጆች እንዳልወለደች መለሰች፡፡ በመቀጠልም ልጆች መውለድ አላስፈለገኝም ምክኒያቱም በአካባቢዬ ተወልደው እንዴት እንደሚያድጉ የጨነቃቸው ብዙ ልጆች አሉ እነርሱን አሳድጋለሁ ብላ መለሰች፡፡ ንግግርዋ ልቤን ነካኝ፡፡ ይች እናት ልጆቻቸውን ወልደው እንክብካቤ ከማያደርጉ እናቶች ይበልጥ የተባረከች ናት፡፡
አንዳንድ እናቶች ድግሞ አሉ የራሳቸውን ልጆች ከወለዱ በኋላ በተጨማሪ ልጆችን በማደጎ ለማሳደግ የሚወስኑ፡፡ እግዚአብሄር እነርሱንም ይባርካቸው፡፡
ሌሎች እናቶች ደግሞ የቻሉትን ያህል ልጆች በየቦታው የሚረዱ፡፡ እግዚአብሄር ይባርካቸው በማለት እንመርቃቸዋለን፡፡
ልጅዋን ወልዳ ከማትንከባከብ እናት ይልቅ ራስዋ ያልወለደችውን ልጅ የምትንከባከብ እናት እውነተኛ እናት ነች፡፡
እናት የወለደችውን ልጅ መንከባከብ በረከት ነው፡፡ እናት ያልወለደችውን ልጅ መንከባከብ ከፍ ያለ በረከት ነው፡፡
ለወለዱት ልጅ ብቻ ሳይሆን ከራሳቸው ቤተሰብ አልፈው ላልወለዱት ልጅ እንክብካቤ የሚያደርጉ እናቶች የተናረኩ ናቸው፡፡ በትምህርት ቤት ፣ በመዋእለ ህፃናት ፣ በሆስፒታሎች ፣ በጎረቤት በመሳሰሉት ላልወለዱት ልጅ እንደልጃቸው አድርገው የሚንከባከቡ እናቶች ክብር ይገባቸዋል፡፡
መልካም መሥራትን ተማሩ፥ ፍርድን ፈልጉ፥ የተገፋውን አድኑ፥ ለድሀ አደጉ ፍረዱለት ስለ መበለቲቱም ተምዋገቱ። ኢሳያስ 1፡17
የወለዱትን ልጅ ከማይንከባከቡ ይልቅ ያልወለዱትን ልጅ እንደ ልጃቸው የሚንከባከቡ የተባረኩ ናቸው፡፡
መልካም የእናቶች ቀን!
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እግዚአብሔር #ሴት #እናትነት #ጌታ #መከተል #ፍቅር #ርህራሄ #ይቅርታ #ቃል #ደግነት #ቸርነት #እግዚአብሔርንመምሰል #ደቀመዝሙር #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment