እኔ
ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ። መዝሙር 17፡15
ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር ክብር ነው፡፡ እግዚአብሄር
ሰውን የፈጠረው በመልኩና በአምሳሉ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ከአርሱ ጋር ህብረት እንዲያደርግ ነው፡፡
ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር ብቻ እንዲረካ ነው፡፡
ስለዚህ ነው ሰው ከእግዚአብሄር ውጭ ምንም እርካታ የሌለው፡፡ ስለዚህ ነው ሰው እግዚአብሄር ብቻ ሊሞላው የሚችል ክፍተት በህይወቱ
ያለው፡፡
መዝሙረኛው የሚለው ይህንን ነው፡፡
ሰዎች በምድር ላይ ያረካናል ብለው ወደ ብዙ ነገሮች
ይሮጣሉ ብዙ ነገሮችን ይፈልጋሉ፡፡ ሰዎች በምድር ላይ ያረካናል የሚሉትን ብዙ ነገሮችን ይሰበስባሉ ነገር ግን ሲያገኙዋቸው አይረኩም፡፡
ሰዎች በምድር ላይ ለመርካት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡
ለእኔ ግን ይላል መዝሙረኛው ሰዎች የሚፈልጉት
ነገር ሁሉ አያረካኝም፡፡ እኔን የሚያረካኝ ግን ይህ ሁሉ ነገር አይደለም ይላል፡፡ ሰዎች የሚፈልጉትን ሁሉ አልፈልግም፡፡ እኔ የምፈልገው
አንተን እግዚአብሄርን ነው እያለው ነው መዝሙረኛው፡፡
እኔ ግን ትክክለኛነቴን ላለመተው ዋጋ እከፍላለሁ፡፡
እኔ ግን አንተን የሚያሳዝን ነገር ላለማድረግ እጠነቀቃለሁ፡፡ እኔ ግን አንተን ለማክበር ሁሉን አድረጋለሁ፡፡ እኔ ግን አንተን ለማክበር ሁሉን እንቃለሁ፡፡ እኔ ግን በእውነት ወደአንተ
እቀርባለሁ፡፡
እኔን የሚያረካኝ ክብርህ ነው፡፡ እኔን የሚያረካኝ
መገኘትህ ነው፡፡ እኔን የሚያረካኝ የአንተ አብሮነት ነው፡፡ እኔን የሚያረካኝ አንተ ነህ፡፡ እኔን የሚያረካኝ አንተን መፈለግ ነው፡፡
እኔን የሚያረካኝ ክብርህን ማየት ነው፡፡
እኔን ሊያጠግበኝ የሚችል ከአንተ ውጭ ከሰማይ
በታች ምንም ነገር የለም፡፡ ሰዎች ለመርካት የሚፈልጉበት ነገር ሁሉ እኔን አያረካኝም፡፡ ሰዎች ለመጥገብ የሚጋደሉለት ነገር ሁሉ
አያጠግበኝም፡፡
እኔን የምረካው ክብርህን ሳይ ብቻ ነው፡፡
እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ ክብርህን ሳይ
እጠግባለሁ። መዝሙር 17፡15
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ክብር #መልክ
#አምሳል #ድህነት #ብፅእና #በረከት
#ቃል #ፀሎት
#አምልኮ #መፈለግ
#መጠማት #መራብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment