Popular Posts

Follow by Email

Monday, April 30, 2018

ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ

እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል። ማርቆስ 16፡15-16
እኛ ሁላችን በጨለማ በነበርነበት ጊዜ ኢየሱስ ወደምድር የመጣው ወንጌልን ሊሰብክና በጨለማ ያሉትን ከእስራት ሊያወጣ ነው፡፡
ከዚያ ዘመን ጀምሮ ኢየሱስ፦ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክ ጀመር። ማቴዎስ 4፡17
አሰብ እኔን እንደላከኝ እንደሂ እልካችሃለሁ ይላ ኢየሰስ ፡፡
ወደ ዓለም እንደ ላክኸኝ እንዲሁ እኔ ወደ ዓለም ላክኋቸው፤ ዮሃንስ 17፡18
እግዚአብሄ መንፈሱን የሰጠን በህይወትና ምሳሌነትና በቃል ወንጌልን እንድንሰብክ ነው፡፡
ኢየሱስም ዳግመኛ፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን፤ አብ እንደ ላከኝ እኔ ደግሞ እልካችኋለሁ አላቸው። ይህንም ብሎ እፍ አለባቸውና፦ መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ። ዮሃንስ 20፡21-22
ኢየሱስ ያለውን ስልጣን ሁሉ ትቶልን የሄደው ወንጌልን እንድንሰብክና ሰዎችን ከጨለማ እንድንታደግ ነው፡፡  
ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ። እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። ማቴዎስ 28፡18-20
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እምነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #ዝራ #የምድርጨው #የአለምብርሃን #የአመፃገንዘብ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ 


Sunday, April 29, 2018

ከጥላቻ ተጠበቁ

እግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ፍቅር በሆነው በእግዚአብሄር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ለፍቅር ነው፡፡ ሰው ዲዛይን የተደረገው ለፍቅር ህይወት ነው፡፡
ፍቅር ስለሰው መልካም ማሰብ መልካም መናገርና መልካም ማድረግ ነው፡፡
ሰው በፍቅር ሲኖር እግዚአብሄር የፈጠረውን አላማ ስለሚፈፅም ደስተኛ ይሆናል፡፡ ሰው በፍቅር ሲኖር እግዚአብሄር ስለሚረዳው በእግዚአብሄር እርዳታ መንገዱ ይቀልለታል፡፡   
ሰው በጥላቻ ሲኖር ግን ህይወቱ ያልተነደፈበትንና ያልተሰራበትን ስራ ስለሚሰራ ህይወቱ ይጨልማል፡፡
ጥላቻ ከማንም በላይ የሚጎዳው የሚጠላውን ሰው ነው፡፡ እንዲያውም ጥላቻ ሌላውን ይገድልኛል ብሎ ራስ መርዝ እንደመጣጣት ነው የሚባለው፡፡
በጥላቻ የሚኖር ሰው በጨለማ ይሄዳል፡፡ በብርሃን አለሁ የሚል ወንድሙንም የሚጠላ እስከ አሁን በጨለማ አለ። ወንድሙንም የሚወድ በብርሃን ይኖራል ማሰናከያም የለበትም፤ ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ አለ፥ በጨለማም ይመላለሳል፥ የሚሄድበትንም አያውቅም፥ ጨለማው ዓይኖቹን አሳውሮታልና። 1ኛ ዮሐንስ 2፡9-11
ጥላቻ ከእግዚአብሄር አይደለም፡፡ በጥላቻም የሚጠቀመው ሰይጣን ብቻ ነው፡፡ የሰይጣን አላማ ሰውን መስረቅ ማረድና ማጥፋት ነው፡፡ ሰይጣን ከመስረቅ ከማረድና ከማጥፋት ሌላ አላማ የለውም፡፡ ሰይጣን ጥላቻ ውስጥ ካስገባን በቀላሉ አላማውን ይፈፅማል፡፡ ከጥላቻ ራሱን ያልጠበቀ ሰው ለዲያብሎስ ፈንታ ሰጥቶት ለምን ሰይጣን በህይወቴ ሰረቀ ፣ አረደና አጠፋ ማለት አይችልም፡፡  
በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት። ኤፌሶን 4፡27
ሰይጣን የመስረቅ የማረድና የማጥፋቱን አላማ የሚያሳካው በሰዎች ውስጥ ጥላቻን በመጨመር ነው፡፡ በሰው ውስጥ የጥላቻን ሃሳብ ካልጨመረ በስተቀር ሰይጣን ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ አይችልም፡፡ ሰይጣን ከጥላቻ ራሱን በሚጠብውቅ ሰው ህይወት ውስጥ እንዳች እድል ፈንታ አይኖረውም፡፡
ኢየሱስ የበደሉትን እንኳን ይቅር በማለት ህይወቱን ከጥላቻ ይጠብቅ ስለነበር ይህንን አለ፡፡
ከእንግዲህ ወዲህ ከእናንተ ጋር ብዙ አልናገርም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ይመጣልና፤ በእኔ ላይም አንዳች የለውም፤ ዮሃንስ 14፡30
ሰይጣን በሰው ውስጥ ጥላን ከጨመረ ደግሞ የማያሰራው ክፋት የለም፡፡ ጥላቻ ላለበት ሰው መግደል ቀላል ነው፡፡ ስለዚህ ነው መፅጽሃፍ ቅዱስ ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው የሚለው፡፡
እኛ ወንድሞችን የምንወድ ስለ ሆንን ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገርን እናውቃለን፤ ወንድሙን የማይወድ በሞት ይኖራል። ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3፡14-15
ማንንም ሰው እንድንጠላ አልተፈቀደልንም፡፡ ልንጠላው የሚገባው ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ የሚመጣውን ሰይጣንነ ብቻ ነው፡፡ እንድንጠላው የሚገባው ሰዎችን ክፋት የሚያሰራውን ሰይጣንን ብቻ ነው፡፡ ልንጠላው የሚገባው ውሸታምና የውሸት አባት የሆነውን በውሸት ሰዎችን የሚያጠላላውን በጥላቻ የሚያገዳድለውን ሰይጣንን ብቻ ነው፡፡
እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና። ዮሃንስ 8፡44
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ጥላቻ #ውሸት #ግድያ #ሰይጣን #ሊሰርቅ #ሊያርድ #ሊያጠፋ #ፍቅር #ምህረት #ይቅርታ #እምነት #ፀሎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል

ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል። እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል። መዝሙር 1፡2-3
እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ለክብሩ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው እርሱን እንዲያመልከውና እንዲታዘዘው ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ቃሉን እንዲሰማና እንዲያደርግ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በቃሉ አንዲኖር ነው፡፡
እግዚአብሄር በሌላ ነገር ሳይሆን በቃሉ ደስ የሚሰኝን ሰው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ሌላን ነገር ሳይሆን ቃሉን የሚሰማን ሰው ይፈልጋል፡፡
አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ። እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ። ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም ተጫወተው። በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው፤ በዓይኖችህም መካከል እንደክታብ ይሁንልህ። በቤትህም መቃኖች በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው። ዘዳግም 6፡5-9    
እግዚአብሄር ሌላ ነገርን ሳይሆን ቃሉን የሚያስብን ሰው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ቃሉን በቀንና በሌሊት የሚያሰብን ሰው ይፈልጋል፡፡
በረከትና ስኬት ያለው በእግዚአብሄር ቃል ውስጥ ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ስናሰላስል እና ስናደርገው ህይወታችን ፈፅሞ ይለወጣል፡፡
የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም። ኢያሱ 1፡8
የእግዚአብሄርን ቃል የሚያሰላስልና የሚያደርግ ሰው እግዚአብሄር ሁልጊዜ ከእርሱ ጋር ይሆናል፡፡ እግዚአብሄር ሙሉ ለሙሉ የተሳካ እንደሆነ ሁሉ የእግዚአብሄርን ቃል የሚያስብና የሚያደርግ ስው በሚሰራው ሁሉ ይከናወናል፡፡
ይህንን ፅሁፍ ሼር ማድረግ ቢወዱ 
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes 

#ቃል #ምስጉን #ሃሳብ #ማሰላሰል #ወንጌል #ደቀመዝሙር #ኢየሱስ #ጌታ #መዳን #አማርኛ #ኢትዮጲያ #አቢይዋቁማ #አቢይ #አቢይዋቁማዲንሳ #ስኬት #ክንውን ###ፌስቡክ #አዋጅ   

Saturday, April 28, 2018

ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ

መምህር ሆይ፥ ከሕግ ማናቸይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት? ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ። ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። ማቴዎስ 22፡36-38
እግዚአብሄር ለክብሩ ፈጥሮናል፡፡
እግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሄር የፈጠረን ለአላማው ነው፡፡
እግዚአብሄር ከምንም ነገር በፊት እንድናስቀድመው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ከምንም ነገር በላይ እንድንሰማው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ከምንም ነገር በላይ እንድንፈልገው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ከምንም ነገር በላይ እንድንፈራው ይፈልጋል፡፡
ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁአችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡15
እግዚአብሄር ከራሳችን በላይ እንድንወደው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ራሳችንን ከእርሱ እንድናስቀድም አያስፈልግም፡፡ እግዚአብሄር ስለእርሱ ነፍሳችንን እንድንክድ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ከደስታችን በላይ እንድንወደው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ከምኞታችን በላይ እንድናስቀድመው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ከፍላጎታችን በላይ እንድንወደው ይፈልጋል፡፡
ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት ስንኳ ሳይቀር ባይጠላ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም። ሉቃስ 14፡26
እግዚአብሄር በህይወታችን ሁለተኛ መሆን አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር በህይወታችን ከሌላ ነገር ጋር መዳበል አይፈልግም፡፡
ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ማቴዎስ 10፡37
እግዚአብሄር ከምንም ነገር በላይ እንድናስቀድመው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ከምንም ነገር በላይ እንድንወደው ይፈልጋል፡፡
መምህር ሆይ፥ ከሕግ ማናቸይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት? ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ። ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። ማቴዎስ 22፡36-38
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፍቅር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #በፍፁምልብ #በፍፁምሃሳብ #በፍፁምነፍስ #በፍፁምሃይል #መውደድ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የቃሉ አካባቢን መጠበቅ

ሰው አካባቢውን ከአየርና ከውሃ ብክለት ለመጠበቅ ታላቅ እንቅስቃሴ ይደረጋል፡፡ ሰዎች የአለምን አረንጓዴነትና ለጤና ተስማሚነት ለመጠበቅ ማንኛውም ነገር ያደርጋሉ፡፡   
ምድርን የሚበክልን ነገር ለምሳሌ የከታላላቅ ፋብሪካዎች የሚወጣውን የተበከለ ጭስ እንዲቀነስ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ፡፡ ምክኒያቱም በቀጣይነት በቆሻሻ አካባቢ ውስጥ የሚኖር ሰው ከመታመምና ከመሞት ሊያመልጥ አይችልም፡፡    
ከዚህ ሁሉ በላይ ግን አለማችንን የሚበክለው እግዚአብሄርን ያለማመንና ጥርጣሬ ነው፡፡ ሰው አካባቢውን በእግዚአብሄር ቃል ካልሞላ እምነት የሚፈጥረውን የእግዚአብሄርበ ቃል ብቻ ካልሰማ እግዚአብሄርን ካላመነ በስተቀር እግዚአብሄርን ደስ ሊያሰኝ ከእግዚአብሄር የሆነውንም ነገር ሊቀበል አይችልም፡፡ ከባቢው ተበላሽቶ እግዚአብሄርን ማመን ካቃተው ሰው የበልጥ ምስኪን ሰው የለም፡፡     
ሰይጣን የሚመጣው ሊሰርቅ ሊያርድ ሊያጠፋ ነው፡፡ ሰይጣን የአስተሳሰብ አካባቢያችንን በመበከል መንፈሳዊ ጤንነታችንን የሚጎዱ ነገሮችን ሊያስፋፋ ይመጣል፡፡    
የሰይጣን የመስረቂያ የማረጃና የማጥፊያ አካባቢዎች አለማመን ፍርሃትና ጥርጣሬ ናቸው፡፡ ሰይጣን ካለማመንና ፍርሃትና ጥርጣሬ ውጭ ሌላ ሃይል የለውም፡፡
ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ አካባቢያችንን በእግዚአብሄር ቃል እንድንሞላና ንፅህናውን ከአለማመን እንድንጠብቅ የሚያስተምረን፡፡ አካባቢያችን በእግዚአብሄር ቃል ስንሞላና የእግዚአብሄርን ቃል ስንሰማ ንፁህ መንፈሳዊ አየርን መተንፈስ እንችላለን፡፡   
የእስራኤል ህዝብ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብ በፍጹምም ነፍስ በፍጹምም ኃይል ለመውደድ አካባቢያቸውን በእግዚአብሄር ቃል እንዲሞሉና ከብክለት እንዲጠብቁና እንዲያፀዱ ተመክረዋል፡፡  
አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ። እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ። ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም ተጫወተው። በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው፤ በዓይኖችህም መካከል እንደክታብ ይሁንልህ። በቤትህም መቃኖች በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው። ዘዳግም 65-9  
የእግዚአብሄር ህዝብ መሪ የነበረው ኢያሱ የእግዚአብሄርን ቃል ለመፈፀም እንዲያስችለው ቃሉን በቀንና በሌሊት እንዲያሰላስልና በቃሉ አካባቢ ውስጥ እንዲኖር ታዟል፡፡  
የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም። እያሱ 18  
እግዚአብሄር እንደልቤ ያለው መዝሙረኛው ዳዊት መዝሙሩን የጀመረው አካባቢውን ከክፋት ሃሳብ ብክለት ስለሚጠብቅና በእግዚአብሄር ቃል ከባቢ ውስጥ ስለሚኖረው ሰው ምስጉንነትና የዘወትር ክንውን በመናገር ነው፡፡  
ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል። እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል። መዝሙር 11-3 ሃዋሪያው ሰው አለምን የማይመስልበትን ብቸኛው መንገድ የሃሳብን አካባቢ በእግዚአብሄር ቃል በማፅዳትና በመጠበቅ እንደሆነ ያስተምራል፡፡    
የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 122
መንፈሳዊ ህይወታችንን ከብክለት ለመጠበቅ በአስተሳሰብ አካባቢያችን የሚፈቀድላቸውና የማይፈቀድላቸው ነገሮች ሊኖሩ እንደሚገቡ መፅሃፍ ቅዱስ በአፅንኦት ያስተምራል፡፡ 
በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤ ፊሊጲስዮስ 48 ስለዚህ ነው ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ምን እንደምትሰሙ ተጠበቁ ያላቸው፡፡ 
አላቸውም፦ ምን እንድትሰሙ ተጠበቁ። ማርቆስ 424
ስለዚህ ነው የእግዚአብሄር ቃል በቤታችን በስልኮቻችን በመኪናችን ልንሰማና ልናነብ የሚገባን፡፡ ለዚህ ነው ባገኘነው አጋጣሚ የእግዚአብሄርን ቃል ከባቢ መፍጠር ያለብን፡፡ ለዚህ ነው የእግዚአብሄርን ቃል ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ መጫወት ያለብን፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ለመስማት ለመረዳትና ለመጠበቅ የእግዚአብሄርን ቃል አካባቢ መፍጠርና በከባቢው ውስጥ መኖር አለብን፡፡  ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ አጥብቀህ አካባቢህን ጠብቅ ያለው፡፡   
ልጄ ሆይ፥ ንግግሬን አድምጥ ወደ ቃሌም ጆሮህን አዘንብል። ከዓይንህ አታርቃት፥ በልብህም ውስጥ ጠብቃት። ለሚያገኙአት ሕይወት፥ ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ነውና። አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና። ምሳሌ 420 22-23  
አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ። እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ። ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም ተጫወተው። በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው፤ በዓይኖችህም መካከል እንደክታብ ይሁንልህ። በቤትህም መቃኖች በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው። ዘዳግም 65-9    
ይህንን ፅሁፍ ሼር ማድረግ ቢወዱ 
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes 

#ቃል #ምስጉን #ሃሳብ #ማሰላሰል #ወንጌል #ደቀመዝሙር #ኢየሱስ #ጌታ #መዳን #አማርኛ #ኢትዮጲያ #አቢይዋቁማ #ፌስቡክ #አዋጅ   

Simply the best

There are more and more temptation to make our lives complicated and bound us by some external factors. But it is always the simpler the better. Let’s see the reasons why simple is always better.
·         Simple is Clear
We are designed to be simple. But men are deceived into complicating their lives. People despise simple things. They only boast on complicated things which they are not created for.  
This only have I found: God created mankind upright, but they have gone in search of many schemes." Ecclesiastes 7:29
We are created to manage simple things. We are limited. We can only manage simple things. We are not good at managing complicated things.  That is the reason the Bible warns us against a multitude of words.
In the multitude of words sin is not lacking, But he who restrains his lips is wise.  Proverbs 10:19
That is the very reason that the Bible equates simplicity with purity and complication with impurity.
All you need to say is simply ‘Yes’ or ‘No’; anything beyond this comes from the evil one. Matthew 5:37
·         Simple is focused
Without focus, we can’t succeed in life. To be focused we must have to have limited responsibilities. We have to put the priority in order to simplify our responsibility and tackle a problem at a time. We live in the world of limited resources. We don’t have all the time and energy we want. We have to decide to give the due priority to the things that we can’t live without.  To utilize our resources effectively, we have to simplify responsibility and thereby our lives.
·         Simple is independent.
When you make your life simple, you will minimize the ways you depend on others. You will be more in control of your life. Simplicity eliminates the things we just want but don’t actually need them. We have to decisively cut the things that we can live without doing them. That makes us to be free to focus on the things we have to.
The want doesn’t deserve our priority. The want can only be done at the expense of the need.
Actually, you can judge a person’s real productivity by the way he simplifies things or complicates them.
Make your life simplified.
For More Articles https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#God #Jesus #life #simplicity #complex #complicated #clear #focus #independence #rejoice #trustgod #grace #salvation #church #testimony #rejoice #preaching #Bible #theword #Abiydinsa #scriptures #abiywakumadinsa

Friday, April 27, 2018

እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ

በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው። እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ። 1ኛ ዜና 16፡10-11
መፅሃፍ ቅዱስ እግዚአብሄርን ስለመፈለግ ግልፅ ነው፡፡
ለምሳሌ መፅሃፍ ቅዱስ ብዙ ብር ያለው ሰው ደስ ይበልው አይልም፡፡ እንዲያውም ባለጠጋ በእግዚአብሄር እንጂ በብልጥግናው እንዳይመካ ነው መፅሃፍ ቅዱስ የሚያስተምረው፡፡
መፅሃፍ ቅዱስ ሃያል በሃይሉ ደስ ይበለው አይልም፡፡ እንዲያውም ሃያል ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የሚደርግ እግዚአብሔር መሆኑን በማወቁና በማስተዋሉ እንጂ በሃይሉ እንዳይመካ መፅሃፍ ቅዱስ ያስጠነቅቃል፡፡
መፅሃፍ ቅዱስ ጠቢብ በጥበቡ ደስ ይበለው አይልም፡፡ እንዲያውም ጠቢብ አለምን ከሰማይ በፍቅር እና በጥበብ በሚያስተዳደር በእግዚአብሄር እንጂ በጥበቡ አይመካ ነው የሚለው፡፡
እግዚአብሄር በምንም እንዳንመካ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር በእርሱ እንጂ በሌላ በምንም ነገር እንዳንመካ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ግን በግልፅ ደስ ሰው እንዲሰኝ የሰጠው ነገር እግዚአብሄርን መፈለግ ብቻ ነው፡፡
ጤነኛ ልብ እግዚአብሄርን ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄርን የሚፈልግ ልብ እየበረታ ይሄዳል፡፡   
እናንተም ትጠሩኛለችሁ፥ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፥ እኔም እሰማችኋለሁ። እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ። ኤርምያስ 29፡12-13
እግዚአብሄርን የሚፈልግ ሰው እግዚአብሄርን ያገኘዋልና ደስ ይበለው፡፡ ሰው በህይወቱ የሚያስፈልገው እግዚአብሄር ነው፡፡ እግዚአብሄርን የሚፈልግ ሰው በህይወቱ የሚያስፈልገውን ብቸኛ ነገር ስለሚያገኝ ደስ ለመሰኘት በቂ ምክኒያት ነው፡፡ እረኛውን እግዚአብሄርን ያገኘ ሰው ሁሉ ሁሉንም ነገር አገኘ፡፡
እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። መዝሙር 23፡1
እግዚአብሄር ሃያል አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄርን የሚፈልግ ሰው ሃያሉን እግዚአብሄርን ያገኛል፡፡ እግዚአብሄርን የሚፈልግን ሰው እግዚአብሄር ያፀናዋል፡፡ እግዚአብሄርን በሚፈልገው ሰው ቦታ የራሱን ብርታት ያሳያል፡፡
ሁልጊዜ በእግዚአብሄር እርዳታ መኖር የሚፈልግ አንዳንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜ መፈለግ አለበት፡፡ በህይወቱ ሳያቋርጥ ክንዱን እንዲገልፅ የሚፈልግ ሰው እግዚአብሄርን መፈለግ ማቋረጥ የለበትም፡፡
በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው። እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ። 1ኛ ዜና 16፡10-11
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ፀሎት #ሁሉንቻይ #ጥበኛ #ሁሉበሁሉ #እግዚአብሔር #እግዚአብሔርንመፈለግ #ፀሎት #የዘላለምህይወት #የእግዚአብሔርፈቃድ #የጊዜው #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ሶስቱ ግልፅ የእግዚአብሄር ፈቃዶች

ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡16-18
እግዚአብሄር ለክብሩ ፈጥሮናል፡፡ እግዚአብሄር እኛን ከመፍጠሩ በፊት በምድር ላይ እንድናደርግለት የፈለገው ፈቃድ ነበረው፡፡ የራሳችንን ፍላጎት ሳይሆን ፈቃዱን በምድር ላይ እንድናደርግ እግዚአብሄር ሰርቶናል፡፡
ሰዎች ሁልጊዜ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለማወቅ ይፈልጋሉ፡፡ ይህ የእግዚአብሄር ፈቃድ ይሆንን ብለው ያስባሉ ይጠይቃሉ፡፡
አእምሮዋችንን በእግዚአብሄር ቃል እንድናድስ የታዘዝነው በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው የእግዚአብሄርን ፈቃድ እንድንለይ ነው፡፡
የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12፡2
በግልፅ የእግዚአብሄር ፈቃድ እንደሆኑ በመፅሃፍ ቅዱሳችን ከተጠቀሱት ነገሮች መካከል እነዚህ ሶስቱ ይገኙበታል፡፡
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤
በነገሮች ብናዝንም በጌታ ደስ እንዲለን የእግዚአብሄርን ፈቃድ እንደሆነ መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡ ሁኔታዎች ቢያሳዝኑንም በጌታ ግን ሁልጊዜ ደስ እንድንሰኝ የእግዚአብሄር ቃል ያዛል፡፡
ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ። ፊልጵስዩስ 4፡6
ሳታቋርጡ ጸልዩ፤
የእግዚአብሄር ልጆች ነን፡፡ ወደእግዚአብሄር መፀለይ እግዚአብሄርን መስማት ከእግዚአብሄር ጋር መነጋገር የእለት ተእለት ተግባራችን ነው፡፡
ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። ፊልጵስዩስ 4፡6
በሁሉ አመስግኑ፤
እግዚአብሄር መልካም አምላክ ነው፡፡ አምላካችን እግዚአብሄር በእርሱ ዘንድ ምንም ክፉ የሌለበት ሁለንተናው መልካም አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር ክፉውን ነገር እንኳን ለመልካም የሚለውጥ አምላክ ነው፡
እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን። ሮሜ 8፡28
በምንም ሁኔታ ውስጥ ብናልፍ እግዚአብሄርን ላለማመስገን ምንም ምክኒያት የለንም፡፡ ሰው እነዚህን በማድረግ አይሳሳትም፡፡ ሰው ግን እነዚህን ባለማድረግ ይሳሳታል፡፡
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡16-18
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ሳታቋርጡጸልዩ #ሁልጊዜደስይበላችሁ #በሁሉአመስግኑ #የእግዚአብሔርፈቃድ #በክርስቶስ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ