የእግዚአብሔር ቃል ቅን ነውና ሥራውም ሁሉ በእምነት ነውና። መዝሙር 33፡4
እግዚአብሄር ቅን ነው፡፡ የእግዚአብሄርም ቃል ቅን ነው፡፡ የእግዚአብሄ ቃል ቀጥተኛ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል እንዳለ ሊቀበሉት የሚገባ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ለውጠውና አሻሽለው የሚቀበሉት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄ ቃል በሞኝዕነት እንዳለ የሚቀበሉት ነው፡፡
ማንም ራሱን አያታልል፤ ከእናንተ ማንም በዚች ዓለም ጥበበኛ የሆነ ቢመስለው ጥበበኛ ይሆን ዘንድ ሞኝ ይሁን። 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡18
እግዚአብሄርን በብልጠት አናገኘውም፡፡ ጠማማ ከሆንን በጠማማነት አንበልጠውም፡፡ እግዚአብሄር ሁለንተናችንን ያውቃል፡፡ እግዚአብሄርን በጠማማነት አናስደንቀውም፡፡
ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ፣ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፣ ከንጹህ ጋር ንጹህ ሆነህ ትገኛለህ ከጠማማ ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ፡፡ መዝሙር 17፡26
ምክኒያቱም እግዚአብሄር እንደ እርግብ የዋህ እንደ እባብ ብልህ ነውና፡፡ (ማቴዎስ 10:16) እግዚአብሄር ማስተዋሉ አይመረመረም፡፡ እግዚአብሄርን ማንም አይበልጠው፡፡
ከሰው ይልቅ የእግዚአብሔር ሞኝነት ይጠበባልና፥ የእግዚአብሔርም ድካም ከሰው ይልቅ ይበረታልና። 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡25
የእግዚአብሄር ነገር በቅንነት ነው፡፡ እግዚአብሄር ጋር ብልጠት አይሰራም፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር ለመኖር ብልጠታችንን ጥለን በቅንነት ብቻ ነው የምንከናወነው፡፡
ሰው ሊታለል ይችላል፡፡ እግዚአብሄርን ግን ማታለል አንችልም፡፡ ሰውን በማታለል ተሳካልን ማለት እግዚአብሄርን በማታለል ይሳካልናል ማለት አይደለም፡፡
የዚህች ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ፊት ሞኝነት ነውና። እርሱ ጥበበኞችን በተንኰላቸው የሚይዝ፤ ደግሞም፦ ጌታ የጥበበኞችን አሳብ ከንቱ እንደ ሆነ ያውቃል ተብሎ ተጽፎአልና። 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡19-20
የእግዚአብሄር መንገድ በእምነት ነው፡፡ ካላመንነው አያምነንም፡፡ ቅን ስንሆን ቅን ይሆንልናል፡፡ ቃሉን ባመንን ቁጥር የፀሎት ቃላችንን ያምናል፡፡ ለቃሉ ቅን በሆንን መጠን ለቃላችን ቅን ይሆናል፡፡ ፀሎታችንን ይሰማል ይመልሳል፡፡
በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። ዮሃንስ 15፡7
ካለቅንነት የዋህነት እና እምነት እግዚአብሄርን ማስደሰት አይቻለም፡፡
ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6
የእግዚአብሄር ቃል የሚሰራው በቅንንት ስንቀበለው ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ለመቀበል የዋህ ካልሆንን ከእግዚአብሄር ጋር እንተላለፋለን፡፡ የእግዚአብሄ ቃል የሚሰራው ቃሉን በሞኝነት የሚቀበሉትንና በቅንነት የሚያደርጉትን ነው፡፡
በእግዚአብሔር ጥበብ ምክንያት ዓለም እግዚአብሔርን በጥበብዋ ስላላወቀች፥ በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ሆኖአልና። 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡21
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#አተረፈ #ንፅህና #ቅንነት #ግልፅ #ንፁህ #ቃል #እምነት #ተንኮል #ጠማምነት #ንጉስ #መክሊት #ኢየሱስ #ጌታ #መፅሃፍቅዱስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ስብከት #እምነት
No comments:
Post a Comment