Popular Posts

Saturday, May 12, 2018

እኔ ግን አልረሳሽም

ጽዮን ግን፦ እግዚአብሔር ትቶኛል ጌታም ረስቶኛል አለች። በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፥ እርስዋ ትረሳ ይሆናል፥ እኔ ግን አልረሳሽም። ኢሳይያስ 49፡14-15
እግዚአብሄር ስለራሱ አዛኝና ርሁርሁነት ሲናገር የእርሱን አዛኝነት ከእናት አዛኝነት ጋር ያመሳሰልዋል፡፡
እናት አዛኝ ርህሩህ ተንከባካቢ ይቅር ባይ መሃሪ ነች፡፡ እግዚአብሄር ታጋሽ ፣ ደግና ቸር ነው፡፡
እግዚአብሔር ርኅሩኅና መሓሪ ነው፥ ከቍጣ የራቀ፥ ምሕረቱም ብዙ ነው፡፡ እግዚአብሔር ለሚታገሡት ቸር ነው። ምሕረቱም በሥራው ሁሉ ላይ ነው። መዝሙር 149፡8-9
ሰው ደግሞ እግዚአብሄር ላይ ሙሉ ለሙሉ እንዲደገፍ ስለተፈጠረ የእግዚአብሄርን የቅርብ ክትትል ይፈልጋል፡፡
እግዚአብሄር ሁሉን ቻይ ሁሉን አዋቂ ነው፡፡
እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም። ዕብራውያን 4፡13
እግዚአብሄር የምድር ዳርቻ ፈጣሪ ነው አይደክምም አይታክትም ማስተዋሉም አይመረመርም፡፡
ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤልም ሆይ፦ መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ? አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ኢሳያስ 40፡27-28
እግዚአብሄር ስለእርሱ እናትነት ደረጃ ሲናገር ከምድር እናትነት እጅግ የላቀ መሆኑን ይናገራል፡፡ እናት የወለደችውን ልጅ ትረሳለችን እያለ ይጠይቃል፡፡ እናተ ብትረሳ እንኳን እርሱ ግን እንደሚራራልንና እንደማይረሳን ይነግረናል፡፡
ጽዮን ግን፦ እግዚአብሔር ትቶኛል ጌታም ረስቶኛል አለች። በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፥ እርስዋ ትረሳ ይሆናል፥ እኔ ግን አልረሳሽም። ኢሳይያስ 4914-15
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እግዚአብሔር #ሴት #እናትነት #ጌታ #መከተል #ፍቅር #ርህራሄ #ይቅርታ  #ቃል #ደግነት #ቸርነት #አልረሳሽም #እግዚአብሔርንመምሰል #ደቀመዝሙር #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት  #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment