እግዚአብሄር በመጀመሪያ የፈጠረን በጤንነት ነው፡፡ ከጥንት እግዚአብሄር ሙላትን ፣ ጤንነትን እና ብርታትን እንጂ በሽታንና ደዌን አልፈጠረም፡፡
በማንኛውም ምክኒያት ጤንነታችንን ብናጣና ብንታመም የእግዚአብሄር የልብ ፍላጎት መፈወሳችን ነው፡፡ እግዚአብሄር ሁልጊዜ ፈውሳችንን ይፈልገዋል፡፡
በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሄር ህዝብ አንዱ ቃልኪዳን የስጋ ፈውስ መሆኑን ስናስብ እግዚአብሄር ህዝቡ እንዲፈወሱና በጤንነትና በብርታት እንዲኖሩ ያለውን በጎ ፈቃድ ያሳያል፡፡
እርሱም፦ አንተ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቀህ ብትሰማ፥ በፊቱም የሚበጀውን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዓቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም፤ እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና አለ። ዘፀአት 15፡26
እግዚአብሔርም ሕማምን ሁሉ ከአንተ ያርቃል፤ የምታውቀውንም ክፉውን የግብፅ በሽታ ሁሉ በአንተ ላይ አያደርስብህም፥ በጠላቶችህም ሁሉ ላይ ያመጣባቸዋል። ዘዳግም 7፡15
በአዲሱም ኪዳን የኢየሱስን አጠቃላይ አገልግሎት ስንመለከት ለህዝቡ ያለውን የእግዚአብሄርን ልብ እንመለከታለን፡፡
እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤ ሃዋሪያት 10፡38
በመሸም ጊዜ አጋንንት ያደረባቸውን ብዙዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ በነቢዩ በኢሳይያስ፦ እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንንም ተሸከመ የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ መናፍስትን በቃሉ አወጣ፥ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ። ማቴዎስ 8፡16-17
ከዘፍጥረት እስከ ራእይ የእግዚአብሄር አላማ መፈወሳችን ነው፡፡
በዘመኑም መጨረሻ የእግዚአብሄር አላማ የሰው ልጆች ፈውስ ነው፡፡
በወንዙም ወዲያና ወዲህ በየወሩ እያፈራ አሥራ ሁለት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበረ፥ የዛፉም ቅጠሎች ለሕዝብ መፈወሻ ነበሩ። የዮሐንስ ራእይ 22፡2
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ
#መሪነት #ቤተክርስትያን #ፈውስ #ስጋ
#ጤንነት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ
#እምነት #ተስፋ #አሁን #ጌታ
#ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment