Popular Posts

Thursday, August 26, 2021

የአርባ ቀን የፈውስ ትምህርት ጉዞ ቁጥር 11

 

ክርስቶስ ስለሃጢያታችን  ከቃሉ በመስቀል ላይ እንደሞተ ከቃሉ ስናይ ደህንነታችንን እንቀበላለን፡፡ እንዲሁም ኢየሱስ ስለሃጢያታችን መገረፉን ከልባችን ስንረዳ በሽታ በእኛ ላይ አቅም አይኖረውም፡፡

የሰው ፈውስ በመስቀል ላይ ተሰርቶ አልቆዋል የሚባለው ስለዚህ ነው፡፡ ኢየሱስ ስለሃጢታታችን እንደገና አይሞትልንም እርሱ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ተሰቀለልን፡፡ የእኛ ፋንታ ለእኔ ነው የተሰቀለው ብለን የተሰቀለውን ማየትና እውቅና መሰጠት ብቻ ነው፡፡

ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል። ዮሐንስ 3፡14-15

እንዲሁም ኢየሱስ ስለበሽታችን እንደገና አይገረፍልንም፡፡ ኢየሱስ ለሃጢያትንና ለሃጢያት ተያያዥ ጥቃቄዎችን በመስቀል ላይ መልስ መልሶ ተፈፀመ ብሎዋል፡፡

አሁን የሚጠበቅብን ነገር የእግዚአብሄር ቃል ስለፈውሳችን የሚለውን መፈለግ ፣ ማንበብ ፣ ማጥናትና ማሰላለስ ብቻ ነው፡፡ ክርስቶስ ስለበሽታችን የሰራውን ስራ የተገረፈውን መገረፍ ማየት ስንጀምር ፈውሳችንን እንቀበላለን፡፡

ፈውስ የሚመጣው በእምነት ነው፡፡ ክርስቶስ በመስቀል ያደረገልንን ነገር ከእግዚአብሄር ቃል ስናይ እምነት ይመጣል፡፡

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17

መጽሃፍ ቅዱስ የእምነት ፀሎት ድውዩን ያድናል ጌታም ያስነሣዋል የሚለን ለዚህ ነው፡፡

የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታም ያስነሣዋል፤ ኃጢአትንም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሰረይለታል። ያዕቆብ 5፡15

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #ፈውስ #ስጋ #ጤንነት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ተስፋ #አሁን #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment