Popular Posts

Thursday, July 20, 2023

አንድነት ውጫዊ ተመሳሳይነት አይደለም

 

አንድነት ተመሳሳይነት አይደለም፡፡ አንድነት በአንድ ጣራ ስር መሰብሰብ አይደለም፡፡ አንድነት ተመሳሳይ ነገር ማሰብ እና ማድረግ አይደለም፡፡ አንድነት ተመሳሳይ ስጦታ መኖር አይደለም፡፡

አንድነትን በተመሳሳይነት መለኪያ ብቻ ከለካነው የማይደረስበት ህልም እናደርገዋለን፡፡ አንድነትን እና ተመሳሳይነትን ግራ ካጋባነው የአንድነት ነገር ተስፋ ያስቆርጠናል፡፡

ብዙ ሰዎች አንድ እየሆኑም አንድ እንደሆኑ የሚጠራጠሩት ስለዚህ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች አንድ ሆነው አንድ ለመሆን በከንቱ የሚጥሩት አንድነት እና ተመሳሳይነትን ግራ ስለሚያጋቡት ነው፡፡

ብዙ ሰዎች አንድ ሆነው በአንድነታቸው የማያርፉት እና የማይረኩት አንድነት ተመሳይነት ስለሚመስላቸው ብቻ ነው፡፡

አንድነት የሚጠይቀው አብሮ መሰብሰብን ሳይሆን የልብ አንድነትን ብቻ ነው፡፡ ምንም ያህል አብረው ቢሰበሰቡ የልብ አንድነት ከሌለ አንድነት የለም፡፡ የልብ አንድነት ካለ ደግሞ ሌላ ምንም አይነት ተመሳሳይነት ባይኖርም አንድነት አለ ማለት ነው፡፡

በየቀኑም በአንድ ልብ ሆነው በመቅደስ እየተጉ በቤታቸውም እንጀራ እየቈረሱ፥ በደስታና በጥሩ ልብ ምግባቸውን ይመገቡ ነበር፤ የሐዋርያት ሥራ 1፡46

በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥ የሐዋርያት ሥራ 2፡1

#ኢየሱስ #ጌታ #አንድ #ፍቅር #አንድነት #ህብረት #አካል #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መተባበር

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa


No comments:

Post a Comment