Popular Posts

Saturday, December 7, 2019

ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌን ነገራቸው፥


እንዲህ ሲል፦ በአንዲት ከተማ እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውንም የማያፍር አንድ ዳኛ ነበረ።
በዚያችም ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፥ ወደ እርሱም እየመጣች፦ ከባላጋራዬ ፍረድልኝ ትለው ነበር።
አያሌ ቀንም አልወደደም፤ ከዚህ በኋላ ግን በልቡ፦ ምንም እግዚአብሔርን ባልፈራ ሰውንም ባላፍር፥
ይህች መበለት ስለምታደክመኝ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ እፈርድላታለሁ አለ።
ጌታም አለ፦ ዓመፀኛው ዳኛ ያለውን ስሙ።
እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን?
እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን? የሉቃስ ወንጌል 18፡1-8

No comments:

Post a Comment