Popular Posts

Friday, August 4, 2023

አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ! ክፍል 7 ባስተላለፋችሁትም ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፤ እንደዚሁም ይህን የሚመስል ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ። የማርቆስ ወንጌል 7፡13 ፈሪሳዊያን እንጅ ታጥቦ ስለ መብላይ ኢየሱስን ከሰሱት፡፡ ኢየሱስም እነርሱ የሚጠቅሱት እጅ መጫን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ውስጥ የሌለለ የሰው ፈጠራ እንደሆነ አስረዳቸው፡፡ ፈሪሳዊያን እግዚአብሔር ያዘዘውን ትእዛዝ ሲያጠናክሩት የእጅ መታጠብ ፈጠሩ፡፡ በብሉይ ኪዳን ህግ ውስጥ ግን እጅ መታጠብ የሚባል ትእዛዝ የትም ቦታ አይገኝም፡፡ ፈሪሳዊያን ከእግዚአብሔር በላይ ለእግዚአብሔር በመቅናት ያቋቋሙት እና እንደእግዚአብሄር ህግ የሚያስተምሩት የሰው ወግ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በራሱ ጠንካራ እና በቂ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ልናጠናክረው እና ልናሻሽለው ስንሞክር ይልቁንም እንሽረዋለን፡፡ የፈሪሳዊያንን ትምህርት መከተል ከዋናው እግዚአብሔር ከሰጠን የክርስትና ትምህርት ውጭ በሆነ በማይጠቅም በሰው ወግ ላይ ጊዜን መፍጀት ነው፡፡ አሁንም በዚህ ዘመን ከሚገባው በላይ ለእግዚአብሔር ተቆርቁሮ እግዚአብሔር ያላዘዘውን በቃሉ ላይ መጨመር ፈሪሳዊነት ነው፡፡ አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa #ኢየሱስ #ጌታ #ፈሪሳውያን #ግብዝነት #የአምልኮትመልክ # #ጻፎች #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ሰዱቃውያን

 

አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ! ክፍል 7

ባስተላለፋችሁትም ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፤ እንደዚሁም ይህን የሚመስል ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ። የማርቆስ ወንጌል 7፡13

ፈሪሳዊያን እንጅ ታጥቦ ስለ መብላይ ኢየሱስን ከሰሱት፡፡ ኢየሱስም እነርሱ የሚጠቅሱት እጅ መጫን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ውስጥ የሌለለ የሰው ፈጠራ እንደሆነ አስረዳቸው፡፡ ፈሪሳዊያን እግዚአብሔር ያዘዘውን ትእዛዝ ሲያጠናክሩት የእጅ መታጠብ ፈጠሩ፡፡ 

በብሉይ ኪዳን ህግ ውስጥ ግን እጅ መታጠብ የሚባል ትእዛዝ የትም ቦታ አይገኝም፡፡ ፈሪሳዊያን ከእግዚአብሔር በላይ ለእግዚአብሔር በመቅናት ያቋቋሙት እና እንደእግዚአብሄር ህግ የሚያስተምሩት የሰው ወግ ነው፡፡ 

የእግዚአብሔር ቃል በራሱ ጠንካራ እና በቂ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ልናጠናክረው እና ልናሻሽለው ስንሞክር ይልቁንም እንሽረዋለን፡፡ 

የፈሪሳዊያንን ትምህርት መከተል ከዋናው እግዚአብሔር ከሰጠን የክርስትና ትምህርት ውጭ በሆነ በማይጠቅም በሰው ወግ ላይ ጊዜን መፍጀት ነው፡፡

አሁንም በዚህ ዘመን ከሚገባው በላይ ለእግዚአብሔር ተቆርቁሮ እግዚአብሔር ያላዘዘውን በቃሉ ላይ መጨመር ፈሪሳዊነት ነው፡፡ 

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ፈሪሳውያን #ግብዝነት #የአምልኮትመልክ # #ጻፎች #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ሰዱቃውያን

No comments:

Post a Comment