አንደኛው የእግዚአብሄር ስም ፈዋሽ አምላክ የሚል ነው፡፡ እግዚአብሄር በመፈወስ ይታወቃል፡፡ እግዚአብሄር ሰዎችን ሙሉ በማድረግ ይታወቃል፡፡
ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ ምስጋናውንም ሁሉ አትርሺ፤ ኃጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፥ ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፥ መዝሙር 103፡2-3
ኢየሱስ በምድር ላይ
በተመላለስ ጊዜ
ከበሽታቸው የፈወሳቸውንና ከአጋንንት እስራት ነፃ ያወጣቸውን ሰዎች ያዩ ሰዎች ሁሉን ደኅና አድርጎአል ብለው መስክረውለታል፡፡
ያለ መጠንም ተገረሙና፦
ሁሉን ደኅና
አድርጎአል፤ ደንቆሮችም
እንዲሰሙ ዲዳዎችም
እንዲናገሩ ያደርጋል
አሉ። ማርቆስ
ወንጌል 7፡37
መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ
የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው (ዮሐንስ 1፡18) ተብሎ እንደተፃፈ የእግዚአብሄር ልብ ያየንበት የኢየሱስ
አገልግሎትን ስንመለከት እግዚአብሄር ሰዎችን ለመፈወስ ምን ያህል እንደሚፈልግ እንመለከታለን፡፡
በአጠቃላይ የኢየሱስን የምድር አገልግሎት እና
ኢየሱስ በሽታን የሚያይበትን መንገድ ስንመለከት እግዚአብሄር ምን ያህል የሰዎችን ጤንነት እንደሚፈልግ እንመለከታለን፡፡
እግዚአብሄር ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ እና በሃይልም
ቀባው፡፡ እግዚአብሄር ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ ብቻ አይደለም በሃይልም ቀብቶታል፡፡ ለሰው ልጆች ፈውስና ነፃ መውጣት እግዚአብሄር
ያለውን ሃይል ሁሉ በኢየሱስ ላይ አፍስሶዋል፡፡
እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ
በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤ ሐዋርያት
ሥራ 10፡38
ኢየሱስንም በታላቅ ቅናት እና ትጋት በያሉበት
ሁሉ በመሄድ ሰዎችን ይፈውስ ነበር፡፡
ይህ የኢየሱስ አገልግሎት የእግዚአብሄርን የመፈወስ
ቅናት ያሳያል፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት
#ቤተክርስትያን #ፈውስ #ስጋ #ጤንነት #አማርኛ
#ስብከት #መዳን
#መፅሃፍቅዱስ #ልብ
#እምነት #ተስፋ
#አሁን #ጌታ
#ሰላም #ደስታ
#አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት
#መሪ
No comments:
Post a Comment