Popular Posts

Friday, February 16, 2018

እረኛዬ እግዚአብሔር

እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። መዝሙር 23፡1
እግዚአብሄር ይመራኛል፡፡ እግዚአብሄርን እያስከተለኝ ነው፡፡ እግዚአብሄር እየመራኝ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን በትጋት ምሪቱን እየሰጠኝ ነው፡፡  የእግዚአብሄርን ምሪት እየተከተልኩ ነው፡፡
እግዚአብሄር ያስብልኛል፡፡ እግዚአብሄር ይጠነቀቅልኛል፡፡ እግዚአብሄር በእኔ ላይ አላማ አለው፡፡ እግዚአብሄር በእኔ ላይ ያለው አላማ ፍቅር ነው፡፡  
እግዚአብሄር ያዘጋጃል፡፡ እግዚአብሄር ያቀርባል፡፡  
እግዚአብሄር አዋቂ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ማስተዋል አይመረመርም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ያስፈልገኛል ያልኩት አንዳንዱ ላያስፈልገኝ ይችላል፡፡ ያስፈልገኛል ብዬ ያሰብኩት ሁሉ አያስፈልገኝም፡፡ እንደሚያስፈልገኝ የሚያውቀው እግዚአብሄር ነው፡፡ እንደሚያስፈልገኝ የሚያውቅው እግዚአብሄር ያስፈልግሃል ካለኝ ያስፈልገኛል፡፡ እንደሚያስፈልገኝ የሚያውቀው እግዚአብሄር ያስፈልግሃል ካላላኝ አያስፈልገኝም፡፡
አንዳንዴ ያስፈልገኛል ብዬ ያሰብኩትን ነገር እስከማጣው ድረስ የሚያስፈልገኝ ይመስለኛል፡፡ አንዳንዱን ነገር እንደማያስፈልገኝ የማውቀው ሳጣው ብቻ ነው፡፡ ያጣሁት ነገር እውነትም እንደማያስፈልገኝ የማውቀው ሳጣው ነው፡፡ ምክኒያቱን እግዚአብሄር እረኛዬ ነው፡፡ እግዚአብሄር የማጣው ነገር የለም፡፡ ያጣሁት ነገር ካለ የማያስፈልገኝ መሆን አለበት፡፡ የሌለኝ ነገር ሁሉ ለጊዜውም ቢሆን የማያስፈልገኝ ነው፡፡
ስለዚህ በእግዚአብሄር እረኝነት በመታመን የሚያሳጣኝ ምንም እንደሌለ በማወቅ የሌለኝ ሁሉ የማያስፈልገኝ ነው እላለሁ፡፡
እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። መዝሙር 23፡1
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #እረኛ #የሚያሳጣኝ #የሚያስፈልገኝ #ያበረታል #ያፅናናል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment