ሰው ፍቅር በሆነው በእግዚአብሄር ተፈጥሮዋል፡፡ እግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ ሰው በፍቅር ተፈጥሮዋል፡፡ ሰው ለፍቅር ተፈጥሮአል፡፡ ሰው የመወደድ እና የመውደድ ፍላጎት አለው፡፡ ሰው የተሰራው በፍቅር እንዲኖር ነው፡፡ ሰው የተቀረፀውና የተፈጠረው በፍቅር እንዲወጣና እንዲገባ ተደርጎ ነው፡፡
ስለዚህ ነው ሰው በተፈጥሮው ፍቅርን ያውቀዋል፡፡ ለፍቅር የተፈጠረው ሰው ፍቅርን ይለየዋል፡፡
እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ። ዮሃንስ 13፡35
ምንም አያውቅም የሚባለ ሰው ፍቅርን ሲያይ ያውቀዋል፡፡ ብዙ የማይረዳው ነገር አለ የሚባለ ሰው ፍቅርን ሲያይ ግን ይረዳዋል፡፡ ፍቅር ሃይል አለው፡፡ ፍቅር ታዋቂ ነው፡፡ ፍቅርን የሚስተው ማንም የለም፡፡
ፍቅር ከእግዚአብሄር ነው፡፡ ፍቅር ርካሽ አይደለም፡፡ ፍቅር በምድር አይገኝም፡፡ ፍቅር ከእግዚአብሄር ብቻ ይገኛል፡፡ ፍቅር በየመንገዱ አይገኝም፡፡ ፍቅር ውድ ነው፡፡ ፍቅር ከእግዚአብሄር ጋር የተገናኙ ሰዎች ጋር ብቻ ይገኛል፡፡ ፍቅር ዝነኛ ነው፡፡ ፍቅር ታዋቂ ነው፡፡ ስለዚህ ነው ኢየሱስ እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ ያለው፡፡
እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ። ዮሃንስ 13፡35
ፍቅር ሃያል ነው፡፡ ለፍቅር መልስ የማይሰጥ ሰው የለም፡፡ ፍቅር የማያንቀሳቅስው ሰው የለም፡፡ በአለም ላይ በጣም አትራፊና ከፍተኛ ምላሽ የሚሰጡ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የሚባሉ አሉ፡፡ ፍቅር ግን ከሁሉ በላይ እጅግ አስተማማኝ ኢንቨስትመንት ነው፡፡ ፍቅር ያሳምናል፡፡ ፍቅር ጉልበት አለው፡፡
እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ። ዮሃንስ 13፡35
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ፍቅር #ምንጭ #መውደድ #ስሜት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ትዕግስት #መንፈስቅዱስ #ማስተዋል #ልብ #መሪ
No comments:
Post a Comment