Popular Posts

Follow by Email

Tuesday, February 6, 2018

በስምህም ጠርቼሃለሁ

አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ። በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም። ኢሳይያስ 43፡1-2
ከየትኛውም ከሚታዩ በረከቶች በላይ የሚያስደስተን ፣ የሚያረካንና ልባችንን የሚያሳርፈው የእግዚአብሄር ከእኛ ጋር የመኖሩ አውቀት ነው፡፡ ሲጀመር ለእግዚአብሄር ክብር ነው የተፈጠርነው፡፡ እኛ የራሳችን አይደለንም፡፡ እኛ የእግዚአብሄር ነን፡፡ የህይወታችን ባለቤት እግዚአብሄር ነው፡፡
እግዚአብሄር አብሮን እንዳለ ካወቅን አንፈራም፡፡ በሚያስፈራ ነገር ውስጥ ለማለፍ የምንደፍረው አግዚአብሄር ከእኛ ጋር እንዳለ ስናውቅ ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን አብሮነት ከተረዳን በሞት መካከል እንኳን ካለፍርሃት እናልፋለን፡፡
በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል። መዝሙር 23፡4
በማይመስል ሁኔታ ውስጥ በፀጥታ የምናልፈው ከምትችሉት በላይ እንድትፈትኑ የማይፈቅ እግዚአብሄር ተብሎ የተጻፈለት ጌታ ከእኛ ጋር እንዳለ በእርሱ እውቅና በከፍታና በዝቅታ እንደምናልፍ ስናውቅ ነው፡፡
ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል። 1ኛ ቆሮንቶስ 10፡13
የምናደርገው ነገር ሃሳቡ የእርሱ እንደሆነ ከተረዳንና እግዚአብሄር አብሮን እንዳለ ስለምናውቅ ምንም መንገዱ አስቸጋሪ ቢሆን እኛም መውጣት መዋጋት መውረስ እንፈልጋለን፡፡ እግዚአብሄር የምናደርገውን ነገር እንደመራን ካላወቅን ግን እኛም አብረን መውጣት አንፈልግም፡፡
እርሱም፦ አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህስ፥ ከዚህ አታውጣን። ዘፀአት 33፡15
ስለዚህ ነው እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ከሆነ ማንም እንደማይቋቋመን መፅሃፍ ቅዱስ የሚያስተምረን፡፡
እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል ሮሜ 8:31
እግዚአብሄርን የማይሰማ ነገር እንደሌለ እግዚአብሄር ሲልከን እና ከእኛ ጋር ሲሆን ሁሉም ነገር እግዚአብሄር በእኛ ወስጥ ለአስቀመጠው አላማ መሳካት ይገዛል፡፡
አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ። በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም። ኢሳይያስ 43፡1-2
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #በስምህ #ጠርቼሃለሁ #ተቤዥቼሃለሁ #የእኔነህ #ሰላም #አትፍራ #ውኃ #እሳት #አትቃጠልም #አይፈጅህም #ስምረት #ፍርድ #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መርካት #ደስታ #ማስተዳደር #እረፍት

No comments:

Post a Comment