Popular Posts

Follow by Email

Sunday, February 11, 2018

ፍቅር አይደለም

እግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በፍቅር ነው፡፡ የተፈጠርነው ለመውደድና ለመውደድ ነው፡፡ የተፈጠርነው በእግዚአብሄርና በሰው ለመወደድና እግዚአብሄርንና ሰውን ለመውደድ ነው፡፡ ፍቅር በህይወታችን በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡
ፍቅር የሚለው ቃል ለብዙ ነገሮች ስለሚጠቅም በጣም ግራ የተጋባ ቃል ነው፡፡
አንድን ነገር ምን እንደሆነ ለመግለፅ ምን እንዳልሆነ መግለፅ ይበልጥ ትርጉም ይሰጠዋል፡፡ ፍቅር ምን እንደሆነ ለመግለፅ ፍቅር ምን እንዳይደለ መግለፅ ለፍቅር ትርጉም ይበልጥ ተጨማሪ መረዳት ይሰጠዋል፡፡
ብዙ ሰዎች ፍቅር የሚመስላቸው መልካም ነገር ማግኘት ሳይሆን መልካም ነገር ማድረግ ነው፡፡ ፍቅር መልካም ለመጠቀም መልካም አጋጣሚ ሳይሆን ለመጥቀም መልካም አጋጣሚ ነው፡፡
ፍቅር በሰው መጠቀም አይደለም፡፡
ፍቅር በሰው መጠቀም አይደለም፡፡ ፍቅር የሰውን ጥንካሬና እድል ተጠቅሞ መለወጥ አይደለም፡፡ ፍቅር ሰውን መጥቀም ነው፡፡ ፍቅር ሰውን ማነሳት ነው፡፡ ፍቅር ሰውን መርዳት ነው፡፡ ፍቅር ሰውን እድለኛ ማድረግ ነው፡፡ ፍቅር ሰውን የተመረቀ ማድረግ ነው፡፡
ፍቅር ከሰው መውሰድ አይደለም፡፡  
ፍቅር መውሰድ አይደለም፡፡ ከሰው የሆነ የሚጠቅም ነገር አይቶ ለመውሰድ መጠጋት ፍቅር አይደለም፡፡ ከሰው ለመውሰድ አላማ ሰውን መጠጋት ብልጠት እንጂ ፍቅር አይደልም፡፡
ፍቅር የራስ ፍላጎትን ማሟላት አይደለም፡፡
ፍቅር የራስን ፍላጎት ማሟያ አይደለም፡፡ ፍቅር የሌላውን ፍላጎት ያማከለ ነው፡፡ ፍቅር ሌላውን መጥቀም ላይ ያተኩራል፡፡
ፍቅር የሰውን ድካም ተጠቅሞ መጠቀም አይደለም፡፡
ፍቅር የሰውን ድካም ይሸከማል፡፡ ፍቅር የሰውን ድካም ይሸፍናል፡፡ ፍቅር የስውን ድካም አያይም ያልፋል፡፡
ፍቅር ያጠፋን አውጥቶ መጣል አይደለም፡፡
ፍቅር የተሻለን ሰው መፈለግ አይደለም፡፡ ፍቅር ሲመች ሲመች አብሮ መሆን አይደለም፡፡ ፍቅር የደከመን አውጥቶ መጣል አይደለም፡፡ ፍቅር ከደካማ ጋር አብሮ መኖር ነው፡፡ ፍቅር ከማይመች ጋር አብሮ መሄድ ነው፡፡ ፍቅር የማይመስለንን ሰው መታገስ ነው፡፡
ፍቅር መታደል አይደለም፡፡
ፍቅር ሌላውን እድለኛ ማድረግ ነው፡፡ ፍቅር ሌላውን ማንሳት ነው፡፡ ፍቅር ሌላውን ማንሳት ነው፡፡ ፍቅር ሌላውን ማሻገር ነው፡፡  
ፍቅር ከሌላው ጋር ራስን በመረዳት ማስተባበር ነው፡፡
እግዚአብሄር በድካማችን ከእኛ ጋር ራሱን አስተባበረ፡፡
ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ሮሜ 5፡8
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ፍቅር #መውደድ #ስሜት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ትዕግስት #መስጠት #ማካፈል #ልብ #መሪ  

No comments:

Post a Comment