Popular Posts

Friday, February 9, 2018

የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነው

የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤ ዕብራውያን 4፡12
የእግዚአብሄር ቃል ህይወት ያለው ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል የሚለውጥ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ሃይል ያለው ነው፡፡  የእግዚአብሄር ቃል የሚሰራ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ሃይልን የተሞላ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ምንም ነገር የመለወጥ ሃይል እና ጉልበት አለው፡፡  
ስለታም ሰይፍ በጣም አደገኛ ነው፡፡ ሁለት ስለት ያለው ሰይፍ ደግሞ ይበልጥ አደገኛ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ሁለት አፍ ካለው ሰይፍ ይልቅ የተሳለ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ሁለት አፍ ካለፍ ሰይፍ ይልቅ ሃያል ነው፡፡
የእግዚአብሄር ቃል በጣም የተሳለ ከመሆኑ የተነሳ ሌሎች ምንም ነገሮች የማይደርሱበትን ቦታ ይደርሳል፡፡ መንፈስና ነፍስ በጣም ተመሳሳይና በቀላሉ ሊለዩ የማይችሉ ነገሮች ናቸው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል በጣም በትክክል የሚለይ በመሆኑ መንፈስንና ነፍስን እንኳን በትክክል ይለያል፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ግን ነፍስንና መንፈስን እስኪለይ ድረስ ይወጋል፡፡
የእግዚአብሄር ቃል የትኛው የነፍስ ሃሳብ የትኛው ደግሞ የመንፈስ ሃሳብ እንደሆነ አጥርቶ ይለያል፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ኢላማውን አይስትም፡፡ የእግዚአብሄር ቃል በትክክል ይለያል፡፡
የእግዚአብሄር ቃል የልብን ስሜትና ሃሳብ ይመረምራል፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ልብን ይመዝናል፡፡ የእግዚአብሄር ቃል የልብን ስሜት ይመረምራል፡፡ የእግዚአብሄር ቃል የሰውን ሃሳብ ይመረምራል፡፡ የእግዚአብሄር ቃል እውነተኛ መርማሪ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ልባቸን ያለበትን ሁኔታ ይነግረናል፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ትክክለኛ መርማሪ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል በልብህ ላይ ችግር አለ ካለ በልብህ ላይ ችግር አለ ማለት ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ጤነኛ ነህ ካለ ጤነኛ ነን ማለት ነው፡፡
እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም። ዕብራውያን 4፡13
ልባችን በሌላ ነገር ፊት ሊደበቅ ይችላል፡፡ በእግዚአብሄር ቃል ፊት ሁሉ ነገር የተገለጠና የተራቆተ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ቃል ፊት የተሰወር ነገር የለም፡፡
የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ እጅግም ክፉ ነው፤ ማንስ ያውቀዋል? እኔ እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመረምራለሁ ኵላሊትንም እፈትናለሁ። ኤርምያስ 17፡9-10
ስለዚህ ነው የእግዚአብሄርን ቃል እንደ መስታወት ተጠቅመን ጉድለታችንን ቶሎ ብለን እንድናስተካካል መፅሃፍ ቅዱስ የሚመክረን፡፡ ስለዚህ ነው የእግዚአብሄር ቃል የሚያሳየንን ማየት ብቻ ሳይሆን ማድርግ እንዳለብትነ መፅሃፍ ቅዱስ የሚያስተምረን፡፡
ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ። ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል፤ ራሱን አይቶ ይሄዳልና፥ ወዲያውም እንደ ምን እንደ ሆነ ይረሳል። ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፥ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፥ በሥራው የተባረከ ይሆናል። ያዕቆብ 1፡22-25
የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤ ዕብራውያን 4፡12
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሄርቃል #ህያው #መንፈስ #ነፍስ #የሚሰራ #ቃልኪዳን #የተሳለ #ጤንነት #ለውጥ #ንፁህ #አትለፍ #ትምህርት # #ፍሬ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አትጨነቁ  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment