Popular Posts

Monday, February 12, 2018

የፍቅር ምንጭ

በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም። ሮሜ 5፡8
ስለ ፍቅር ክብር ስናጠና ፍቅር እጅግ የከበረ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ እግዚአብሄር እንኳን ፍቅር ነው በሚል ነው የተገለፀው፡፡ ስለፍቅር ክብር ስናስብ ይህ ፍቅር የሚባለው ነገር ይቻል ይሆንን ብለን ልናስብ እንችላለን፡፡
ፍቅር ይቻላል፡፡ ፍቅር የሚቻለው በእኛ አይደለም፡፡ በራሳችን ፍቅርን ማድረግ አንችልም፡፡ በበራሳችን ጉልበት በፍቅር መኖር አይታሰብም፡፡
ፍቅር እግዚአብሄር ነው፡፡ የፍቅር ምንጩ እግዚአብሄር ነው፡፡ በእግዚአብሄር የተወደደ ሰው ብቻ ነው በፍቅር የሚኖረው፡፡ የእግዚአብሄርን ፍቅር ያልተረዳ ሰው ፍቅር ሊኖረው አይችልም፡፡ በእግዚአብሄር እንደተወደደ የማያውቅ ሰው ፍቅር ለእርሱ እንግዳ ነገር ነው፡፡ በእግዚአብሄር የተወደደ ሰው ሰውን ሊወድ ይችላል፡፡ ከእግዚአብሄር ፍቅርን የተቀበለ ሰው ለሌላው ፍቅርን ሊሰጥ ይችላል፡፡ የተወደደ ሰው ለመውደድ ጉልበትን ያገኛል፡፡
በእግዚአብሄር የሚኖር በፍቅር ይኖራል ፡፡ በፍቅር የማይኖር እግዚአብሄርን አላየውም አላወቀውም፡፡
በእኛ ዘንድ ፍቅር ከተገኘ ምንጩ እግዚአብሄር ነው፡፡
ከእግዚአብሄር የሆነ ሰውና ከእግዚአብሄር ያልሆነ ሰው የሚለየው በፍቅር ነው፡፡ በእግዚአብሄር የተነካ ሰውና ያልተነካ ሰው የሚያስታውቀው በፍቅር ነው፡፡ በእግዚአብሄር የተለወጠ ሰውና ያልተለወጠ ሰው የሚታወቀው በፍቅር ነው፡፡
ማንኛውም አካሄዳችን ከእግዚአብሄር ይሁን አይሁን መመዘኛው በፍቅር መደረጉና አለመደረጉ ነው፡፡ በፍቅር የተደረገ ነገር ሁሉ ከእገዚአብሄር ነው በፍቅር ያልተደረገ ነገር ሁሉ ከእግዚአብሄር አይደለም፡፡
በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም። ሮሜ 5፡8
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ፍቅር #ምንጭ #መውደድ #ስሜት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ትዕግስት #መንፈስቅዱስ #ማስተዋል #ልብ #መሪ  

No comments:

Post a Comment