እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርስዋም ደስ ይበለን። መዝሙር 118፡24
ህይወት የእግዚአብሄር ስጦታ ነው፡፡ እያንዳንዱ ቀን የእግዚአብሄር በረከት ነው፡፡
ስለለመድነውና ለአመታት ከእንቅልፋችን ስለተነሳን እኛ በራሳችን የተነሳን ይመስለናል እንጂ በህይወት ያለነው በእያንዳንዱ ቀን እግዚአብሄር ደግፎ ስላነቃን ነው፡፡
እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፤ እግዚአብሔርም ደግፎኛልና ነቃሁ። መዝሙር 3፡5
እግዚአብሄር የሰጠንን ቀን በሚገባ መያዝ ሰጪውን ማክበር ነው፡፡ በተሰጠንን በዚህ ቀን ሰጪውን ማማረር እግዚአብሄርን ደስ አያሰኘውም፡፡
ነገ እናገኘዋለን እንደርስበታለን ብለን ስለምናስበው ተስፋ ዛሬን ማጣጣልና ማንቋሸሽ የሰጪውን ስጦታ በሚገባ አለማክበር ነው፡፡
ዛሬን የተሰጠንን ስጦታ በሚገባ ሳንይዝ የነገንና የነገ ወዲያን ህይወት ዛሬ ለመኖር መሞከር እግዚአብሄርን የእግዚአብሄርን ስጦታ አላግባብበ መጠቀም ነው፡፡
ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል። ማቴዎስ 6፡34
ዛሬ እግዚአብሄር የሰጠንን አዲስ ቀን ችላ ብለን ባለፈው ስህተታችን እና ውድቀታችን ለመኖር መሞከር ስጦታውን በትክክል አመጠቀም ነው፡፡ ያለፈውን ህይወታችንን አሁን እንደገና ለማስተካካለ መሞከር የማይቻል ከንቱ ድካም ነው፡፡
ዛሬ መኖር የምንችለው ዛሬን ነው፡፡ ትላንት ወደኋላ ተመልሰን ልናስተካክልው የማንችለው ትዝታ ነው፡፡ ነገ ምን እንደሆነ የማናውቅው ልንመካበታን የማንችለው ተስፋ ነው፡፡ ባለንበት ደረጃና ባለን ነገር ዛሬን በሚገባ ከኖርንና በዛሬ ደስ ከተሰኘን ትላንትናና ነገ ትክክለኛ ቦታቸውን ይይዛሉ፡፡
ዛሬን ግን እንደእግዚአብሄር ስጦታ በከፍተኛ ዋጋ ካልያዝንው ዛሬን እናጣዋለን፡፡ ዛሬ ላይ ትላንትን መኖር አንችልም፡፡ በህይወታችን የምናስባቸው ነገሮች ቢሆኑም እንኳን ነገ ላይ ዛሬን መልሰን መኖር አንችልም፡፡ ዛሬን አጣጣልነውም ፣ ደስ ተሰኘበትም ፣ ተጠቀምንበትም ፣ ገፋነውም ዛሬ ተመልሶ አይመጣም፡፡
ዛሬ ፍፁም ስጦታ ነው፡፡ ዛሬን ምንም አንጨምርበትም ምንም አንቀንስበትም፡፡ ማድረግ የምንችለው ብቸኛ ነገር በዛሬ ደስ መሰኘት ነው፡፡
እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርስዋም ደስ ይበለን። መዝሙር 118፡24
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #ዛሬ #ነገ #ትላንት #ትዝታ #ተስፋ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ሃሴት #ደስታ #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment