Popular Posts

Friday, February 2, 2018

የህይወት ጥያቄ አንድ መልስ የለውም

የህይወት ጥያቄ አንድ መልስ የለውም፡፡ የህይወት ጥያቄ ብዙ ነው፡፡ የህይወት ጥያቄ ውስብስብ ነው፡፡ ነገር ግን የህይወት ጥያቄ ሁሉ መልስ አለው፡፡ ውስብስብ ለሆነ የህይወት ጥያቄ ቀላል መልስ መመለስ ሞኝነት ነው፡፡ ለዘርፈ ብዙ የህይወት ጥያቄ አንድ መልስ ለመመለስ መሞከር ስህተት ነው፡፡   
የህይወት ጥያቄ አንድ መልስ የለውም፡፡ የህይወት ጥያቄ አንድ ነጠላ ስላይደለ መልሱም አንድ ነጠላ ሊሆን አይችልም፡፡
የህይወት ጥያቄን አንዴ መልሰን የምንገላገለው አይደለም፡፡ የህይወት ጥያቄ ለረጅም ጊዜ እየፈታን እየፈታን የምንሄደው ነው፡፡ በእግዚአብሄር ላይ ከመደገፍ ይልቅ የህይወት ጥያቄን በራሳችን ለመፍታትና ለመገላገል መሞከር እግዚአብሄርን ደስ አያሰኘውም፡፡ እግዚአብሄር ስለ ጥያቄያችን በእያንዳንዱ ቀን ሁሌ እንድንደገፍበት ይፈልጋል፡፡  
ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል። ማቴዎስ 6፡34
እንዲህ አደርጋለሁ፤ ጐተራዬን አፍርሼ ሌላ የሚበልጥ እሠራለሁ፥ በዚያም ፍሬዬንና በረከቴን ሁሉ አከማቻለሁ፤ ነፍሴንም፦ አንቺ ነፍሴ፥ ለብዙ ዘመን የሚቀር ብዙ በረከት አለሽ፤ ዕረፊ፥ ብዪ፥ ጠጪ፥ ደስ ይበልሽ እላታለሁ አለ። ሉቃስ 12፡18-19
የሰው ባህሪ ለህይወት ጥያቄ አንድ መልስ አግኝቶ ቢያርፍ ደስ ይለዋል፡፡ የህይወት ጥያቄ ግን እንደዚያ አይመለስም፡፡ ሰው ለውስብስቡ የህይወት ጥያቄ ቀላል መልስ መልሶ እፎት ቢል ደስተኛ ነው፡፡ ነገር ግን የህይወት ጥያቄ እንደዚያ አይመለስም፡፡ ወይም ደግሞ ሰው አንዴ የህይወትን ጥያቄ መልሶ ሁለተኛ ባይጠየቅ ደስታው ነው፡፡ የህይወት ጥያቄን ለመመለስ ረጅም ቀጣይነት ያለው ስራን ይጠይቃል፡፡
ከአዛሄልም ሰይፍ ያመለጠውን ሁሉ። ኢዩ ይገድለዋል፤ ከኢዩም ሰይፍ ያመለጠውን ሁሉ ኤልሳዕ ይገድለዋል። 1ኛ ነገሥት 19፡17
ለተሳካ ህይወት ጥበብ ወሳኝ ስለዚህ ነው፡፡ ጥበብ ካለን ለያንዳንዱ የህይወት ጥያቄ መልስ መስጠት እንችላለን፡፡
የህይወት ጥያቄ ብዙ ስለሆነ ብዙ ጥበብ ያስፈልገናል፡፡ ብዙ ጥበብ ባገኘን መጠን ጥያቄዎችን የመፍታት አቅማችን ይጨምራል፡፡ ጥበብን በልግስና የተቀበለ ሰው ጥያቄዎችን ለመመለስ የተሻለ አቅም ይኖረዋል፡፡
ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል። ያዕቆብ 1፡5
የህይወት ጥያቄ ዘርፈ ብዙ ስለሆነ ጥበብም ዘርፈ ብዙ ነው፡፡ ለዘርፈ ብዙ ተግዳሮት ልዩ ልዩ ጥበብ ይጠይቃል፡፡  
ብዙ ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት ትታወቅ ዘንድ፤ ኤፌሶን 310
ሰይጣን የሚመጣው በተለያዩና በብዙ አቅጣጫዎች ነው፡፡ ሰይጣን በግል ህይወት ፣ በስራ ፣ በቤተሰብ ፣ በትዳር ፣ በቤተክርስትያን ፣ በጓደኛ ፣ በዘመድ በመሳሰሉት ሁሉ  ይምጣል፡፡ አንዱን የፈታችሁበት መንገድ ለሌላው አይሰራም፡፡ ለአንዱ የመለሳችሁት መልስ ለሌላው ትክክለኛ መልስ አይሆንም፡፡
በመፀለይ የሚመለስ ጥያቄ አለ ፣ ቃሉን በመታዘዝ የሚመለስ ጥያቄ አለ ፣ የእግዚአብሄርን ቃል በማሰላለስ የሚመለስ ጥያቄ አለ ፣ የእግዚአብሄርን ቃል በመናገር በማወጅ /ኮንፌስ/ በማድረግ የሚመለስ ጥያቄ አለ ፣ ሰውን በመውደድ የሚመለስ ጥያቄ አለ ፣ ሰውን ይቅር በማለት የሚመለስ ጥያቄ አለ ፣ ጌታን በማገልገል የሚመለስ ጥያቄ አለ ፣ በትግስት በመጠብቅ የሚመለስ ጥያቄ አለ ፣ ተግቶ በመስራት የሚመለስ ጥያቄ አለ፡፡ ለጥያቄ ሁሉ አንድ መልስ ብቻ እንዳለው ማሰብ ሞኝነት ነው፡፡  
ስለዘህ ነው እግዚአብሄር ለምናልፍበት ነገር የሚያስፈልገውን ጥበብ እንዲሰጠን ዘወትር ልባችንን ለእርዳታ ወደ እግዚአብሄር ማንሳት ያለብን፡፡
ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም። ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል። ያዕቆብ 1፡2-5
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልዩልዩ #በልግስና #ብዙ #ጥበብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ማስተዋል #እምነት #ፈተና #ፀሎት #ጌታ #የእግዚአብሄርቃል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment