Popular Posts

Thursday, February 22, 2018

እሳት እንደሚያቀጣጥል

ስለዚህ ምክንያት፥ እሳት እንደሚያቀጣጥል ሰው፥ እጆቼን በመጫኔ በአንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ስጦታ እንድታነሣሣ አሳስብሃለሁ። 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፡6
ለጌታ መኖርና ጌታን ማገልገል እጅግ ከፍተኛው እድልና ህይወታችንን ሳንሰሰት ልንሰጠው የሚገባን ትልቅ ነገር ነው፡፡ ጌታን እንደማገልገልና ለጌታ እንደመኖር እጅግ የተከበረ ዘላለማዊ ዋጋ ያለው ነገር የለም፡፡
ለጌታ መኖርና ጌታን ማገልገል ብዙ እንቅፋቶች አሉበት፡፡ አታልፍም አትሄድም የሚሉ ብዙ ድምፆች በአካባቢያችን አሉ፡፡ በቃህ ተወው ብርር ብለህ ጥፋ ጥፋ የሚሉ ብዙ ድምፆች አሉ፡፡ አንተ ከማን ትበልጣለህ ምንም አታመጣም በሚሉ በብዙ ድምፆች መካከል እግዚአብሄርን እናገለግላለን፡እነዚህን ድምፆች እህህ ብለን ብንሰማ በህይወትና በአገልግሎት አንዘልቅም ነበር፡፡
እሳት ምንም ሃያል ቢሆን በአመድ ስር ከተዳፈነና በአመድ ከተሸፈነ ለምንም አይጠቅምም፡፡ በልባችን ያለውን እሳት ሊያደበዝዝ ብሎም ሊያጠፋ የሚመጣውን ነገር ነቅተን እሳታችንን ካልጠበቅነው ሳናውቀው እሳታችን በማጣት አገልግሎታችንንና ህይወታችን ልናጣ እንችላለን፡፡
በህይወታችን ያሉ ታላላቅ ነገሮች መልካምነትና ፍቅር በተለያየ ተግዳሮት ሊዳፈኑ ይችላሉ፡፡
ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ፤ ዕብራውያን 10፡24
ለብዙዎች መነሳትና መለወጥ እግዚአብሄር በውስጣችን ያስቀመጠው ፀጋ ሊዳፈንና ሊደበዝዝ ይችላል፡፡ እግዚአበሄር በሚያስፈልገው ሃይል አስታጥቆን ሳለ ነገር ግን እሳታችንን ካጣነው አገልግሎታችንን በአገልግሎታችንም የምናፈራውን ፍሬ እናጣዋለን፡፡   
እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና። 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፡7
ስለዚህጅ ነው ሃዋሪያው ጳውሎስ በክርስቶስ ልጁ የሆነውን ጢሞቴዎስን የሚያነቃቃው፡፡ ጢሞትዮስ ምንም መንፈሳዊ ስጦታዎች ቢኖሩትም እሳቱ ከጠፋ ለምንም የማይጠቅም ይሆናል፡፡
እሳት ደግሞ በየጊዜው ካልተራገበ ይጠፋል፡፡ እሳት ካልተነቃቃ አንዴ ስለተቀጠጣለ ብቻ አይቆይም፡፡
በህይወትና በአገልግለዖት ከሃይል ወደ ሃይል ለመሄድ እሳታችንን ከሚያዳፍኑ ነገሮች ህይወታችንን ልንጠብቅ እሳታችንን ለማቀጣጠል የሚጠይቀውን ሁሉ ማድረግ ሃላፊነታችን ነው፡፡  
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እሳት #ህብረት #ቃል #መቀጣጠል #ክብር #አገልግሎት #ፀጋ #መዋረድ #መርካት #ፀጋ #እውቀት #ኢየሱስንተመልክተን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #እምነት #ታላቅነት #ማገልገል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment