Popular Posts

Friday, February 2, 2018

ክፉውን አትቃወሙ

እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ክፉውን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፤ ማቴዎስ  5፡39
በህይወቱ የሚያየውን ክፉ ሁሉ በክፉ ለመመለስ የሚያስብ ሰው የክርስትናን ህይወት በሚገባ አልተረተዳውም፡፡
በአለም የሚኖሩ ሰዎች ውድድራቸው በክፋት ነው፡፡ ክፉ ያደረገ ሰው ይከበራል፡፡ እጅግ ክፉ ያደረገ ሰው ደግሞ ይበልጥ ይከበራል፡፡ በአለም ያለው ውድድር የእኔነት ውድድር ነው፡፡ ሰው በአለም እኔነቱን ለማሳየት ክፉን ሲያደርግ ክፋትን ሲጨምር በክፉ ሲበልጥ ይታያል፡፡
በአለም ያለ ሰው አሸናፊነቱ ክፉን በክፉ በማሸነፍ ነው፡፡ ክፉን በክፉ የሚያሸነፈ ሰው ይከበራል፡፡ በአለም ክፉን በክፉ አለማሸነፍ ደካማነት ነው፡፡ በአለም ክፉን በእጅግ ክፉ ማሸነፍ ደግሞ ጀግንነት ነው፡፡ በአለም ሰዎች በክፋታቸው ይመካሉ፡፡
በእግዚአብሄር ቤት ግን የሚያስከብረው ክፉን የመቋቋም ችሎታ ነው፡፡ በክርስትና የሚያስከብረው ክፉን የምናሸነፍበትን ፀጋ ማሳየት መግለፅ ነው፡፡ በክርስትና አሸናፊነት ክፉ ያደረጉበትን ሰው በክፋቱ ሳይሸነፉ መልካም ሲያደርጉለት ነው፡፡
ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ። ሮሜ 12፡21
በአለም በክፉ የሚሸነፍ ሰው የተለመደ ነው፡፡ ማንም መንገደኛ በክፉ ይሸነፋል፡፡ በክርስትና በክፉ የሚሸነፍ ሰው ደካማ ነው፡፡
ጠላትህ ግን ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና። ሮሜ 12፡20
በእግዚአብሄር ቤት ከአለም ሰዎች የተለየ በእኛ የሚሰራ ፀጋ እንዳለን የምናሳየው ክፉን በመልካም በመለመለስ ነው፡፡ ከሌሎች የተለየ የእግዚአብሄር ሃይል በውስጣችን እንደሚሰራ የምናሳየው በክፉ ባለመሸነፍ ነው፡፡
ከአለምና ከምድራዊ የተለየ የተሻለ መንገድ የምናሳየው በክፉ ባለመሸነፍ ነው፡፡ የክፉን ህሊናውን የምንነካው ለክፋቱ ክፋት ባለመመለስ ነው፡፡ ክፉን የምናነቃው ለክፋቱ ክፋት ሲጠብቅ መልካምን በመመለስ ነው፡፡ ክፉ የሚደነግጠውና ሌላ አሰራርና ሌላ መንግስት እንዳለ የሚያስበው ክፉን በመልካም የሚመልስ ሰው ሲገጥመው ነው፡፡
በክፉ የማይሸነፍ በመልካም የሚያሸነፍ የተለየ የሚያስችል ሃይል እና ፀጋ እንዳለን የምንመሰክረው በክፉ ባለመሸነፍ በመልካም በማሸነፍ ነው፡፡ ክፉ ይህንም የተለየ ፀጋ እንዲቀናበትና ለራሱ እንዲፈልገው የሚያደርገው ክፉን በመልካም የሚሸንፍ ልዩ ሃይል እንዳለን ሲያይ ነው፡፡   
ሰው እናንተ የተለያችሁ ሰዎች ናችሁ የእናንተ ጌታ የእኔ ጌታ እንዲሆን እንፈልጋለሁ የሚለው ክፉን በመልካም የምናሸንፍበትን ከዚህ አለም ያልሆነ መልኮታዊ ሃይል ሲያይ ነው፡፡
እንዲከስህም እጀ ጠባብህንም እንዲወስድ ለሚወድ መጎናጸፊያህን ደግሞ ተውለት፤ ማንም ሰው አንድ ምዕራፍ ትሄድ ዘንድ ቢያስገድድህ ሁለተኛውን ከእርሱ ጋር ሂድ። ማቴዎስ 5፡40-41
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #ፀጋ #የሚያስችልሃይል #ብቃት #የእግዚአብሄርችሎታ #የእግዚአብሄርሃይል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ፅድቅ #እግዚአብሄርንመምሰል #ራስንመግዛት #ልብ #ምስክርነት 

No comments:

Post a Comment