Popular Posts

Tuesday, February 20, 2018

ህይወት ስጦታ ነው

አንዳንድ ጊዜ የህይወትን ሃላፊነት ስንመለከት ስጦታነቱን አንረሳለን፡፡ ነገር ግን ህይወት ሃላፊነት ብቻ ሳይሆን እንድንደሰትበት የተሰጠን ስጦታ ነው፡፡
በህይወት ነገሮችን ለማግኘት ጠንክረን እንሰራለን፡፡ በህይወት የሆነ ቦታ ለመድረስ እንተጋለን፡፡ በህይወት እከሌ ለመሆን እንጥራለን፡፡
በህይወት አንድ ነገር ለማድረግ እንደምንጠረው ሁሉ በደረስንበትን ግኝት ግን ለመደሰት ጊዜ አንወስድም፡፡
በህይወት አንድ ቦታ ለመድርስ እንደምንጠረው በደረስንበት ቦታ ለመደሰት ጊዜ አንወስድም፡፡
በህይወት እከሌ ለመሆን እንለፋለን የሆነውን ግን ጊዜ ወስደን ለማጣጣም ጊዜ ከሌለን ህይወት ሙሉ አይሆንም፡፡
በእንዱ ግኝት በአል ለማድርግና ለመደሰት ጊዜ ሳንወስድ ግኝቱ አሽቀንጥረን ጥለን ለሌላ ግኝት እንዘረጋለን፡፡
ህይወት እየቆዩ እያጣጠሙት የሚደሰቱበት እንጂ ምንም ደስታ የሌለው የሸክምና የስራ ብዛት አይደለም፡፡
እነሆ፥ እኔ ያየሁት መልካምና የተዋበ ነገር ሰው እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ፥ ከፀሐይ በታችም በሚደክምበት ድካም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ ነው፤ ይህ እድል ፈንታው ነውና። መክብብ 5፡19
የህይወት ግኝት ወይም የህይወት ስኬትን ሙሉ የሚያደረግው ስኬተን ማጣጣም ሲቻል ብቻ ነው፡፡ ሰው ስኬታማ ለመሆን በብዙ ነገሮች እንደሚሰለጥነው ሁሉ ስኬቱን ረጋ ብሎ ለማጣጣምና በስኬቱ ለመደሰት መማር አለበት፡፡ የስኬትን መንገድ ማወቅ መረዳት ብቻ ሳይሆን ስኬቱን እንዴት እንደምናጣጥመው መማር ስኬቱን ሙሉ ያደርገዋል፡፡  
እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ ባለጠግነትንና ሀብትን መስጠቱ፥ ከእርስዋም ይበላና እድል ፈንታውን ይወስድ ዘንድ በድካሙም ደስ ይለው ዘንድ ማሠልጠኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። መክብብ 5፡19
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #መደሰት #ስኬት #ህይወት #ስጦታ #በረከት #ስኬት #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መርካት #ደስታ #ማስተዳደር #እረፍት

No comments:

Post a Comment