አንተ
የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሳ ክርስቶስም ያበራልሃል ኤፌሶን 5:14
አንዳንዴ አሁን ልተኛ ብለን በውሳኔ አውቀንና
ፈቅደን እንተኛለን፡፡ አንዳንዴ ግን እንቅልፍ ተጫጭኖን ሳናውቀው ተኝተን እንገኛለን፡፡
መተኛታችንን ሊያቆመው የሚችለው ምንም ነገር የለም፡፡ ምክኒያቱም የተኛነው አውቀን
አይደለም፡፡ ሳናስበው በድንገት አንቀላፍተን ለመተኛታችን ምክኒያቱ ወይ ብዙ መብላት ወይ ብዙ መጠጣት ሊሆን ይችላል፡፡ ቀላል ያለ
ህይወት እንቅልፍ እንቅልፍ እንዲለን እንዳንነቃ ያደርገናል፡፡ የምናደርጋቸው መጠናቸውን ያለፉ ነገሮች እንዲደካክመን እንቅልፍ እንቅልፍ
እንዲለንና እንድንተኛ ያደርጉናል፡፡
ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ
ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና። ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ
ጦር እንልበስ። በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት
አይሁን፤ ሮሜ 13፡11-13
መንቃት ግን በጣም ወሳኝ የሆነ ነገር ነው፡፡ ስንነቃ እናያለን፡፡ ስንነቃ እናስተውላለን፡፡
ስንነቃ እንወስናለን፡፡ ስንነቃ እንሰራለን፡፡ ስንነቃ እንንቀሳቀሳለን፡፡ ስንነቃ ነገሮችን እንለውጣለን፡፡ ስንነቃ ራችንን መከላከል
እንችላለን፡፡
ካልነቃን እንሰረቃለን፡፡ ካልነቃን እንደክማለን፡፡ ካልነቃን እንበለጣለን፡፡ ካልነቃን
እንታለላለን፡፡
አይ እኔ አልተኛሁም አላንቀላፋሁም ልንል እንችላለን፡፡ ነገር ግን የተለያዩ የመንቃት
ደረዎች አሉ፡፡ ነቅቻለሁ ያለነው ደረጃ ማንቀላፋት ሊሆን ይችላል፡፡
ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ተመልሶ ከእንቅልፉ እንደሚነቃ ሰው አነቃኝ።
ዘካርያስ 4፡1
ዘካርያስ ከመላኩ ጋር ይነጋገር ነበር፡፡ ከመላኩ ጋር ይነጋገር የነበረውን ዘካሪያስን
መላኩ ከእንቅለፉ እንደሚነቃ ሰው አነቃው፡፡ ዘካሪያስ መላኩ እስከሚያነቃው ድረስ በእንቅልፍ ውስጥ እንደነበረ አላወቀም፡፡ ዘካርያስ
መላኩ እስከሚያነቃው ድረስ እንደዚያ ያለ የመንቃት ደረጃ እንዳለ አላወቀም ነበር፡፡
ነቅቻለሁ ብትሉም ከዚህ በላይ የመንቃት ደረጃ እንዳለ ማወቅ አለባችሁ፡፡ የእናንት
የመነቃት ደረጃ የመንቃት የመጨረሻው ደረጃ አይደለም፡፡ ጌታ ሲያነቃችሁ ከእንቅልፍ እንደነቃችሁ ነው እንደ አዲስ የምትነቁት፡፡
በመጠኑ ኑሩ ንቁም፥ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያጋሳ አንበሳ ይዞራልና፤1ኛ
ጴጥሮስ 5፡8
አንተ የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሳ ክርስቶስም ያበራልሃል ኤፌሶን 5:14
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ #ፀሎት #ልመና #ምልጃ #ምስጋና #ውዳሴ #በመጠኑ #እንደፈቃዱ #መጠየቅ #መንበርከክ #ይቃትታል #መንፈስቅዱስ #እንዲሰማን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment