የምትድነው ነፍስ
ነፍስ እውቀት የሌለባት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤
ምሳሌ 19፡2
ነፍስ የእውቀት ማእከል ነች፡፡ ሃሳባችን ቅርፅን
የሚይዘው በነፍስ ውስጥ ነው፡፡ አውጥተን አውርደን ውሳኔን የምንወስነው በነፍሳችን ነው፡፡
ነፍስ የተሰራችው ለእውቀት ነው፡፡ ነፍስ የምትንቀሳሰቀሰው
በእውቀት ነው፡፡ ነፍስ ትክክለኛውን እውቀት ካገኘች ትለመልማለች ታፈራለች፡፡ ነፍስ ትክክለኛውን እውቀት ካላገኘት ትቅበዘበዛለች
እረፍትም ታጣለች፡፡
ካለ እግዚአብሄር እውቀት ነፍስ አደጋ ላይ ትወድቃለች፡፡
ካለ እውቀት ነፍስ የተሰራችበትን አላማ መፈፀም ያቅታታል፡፡ ካለ እውቀት የሆነች ነፍስ በእግዚአብሄር ስራ ላይ እንቅፋት ትሆናለች፡፡
ካለ እውቀት የሆነች ነፍስ እግዚአብሄር ያዘጋጀላትን አላማ ትስታለች፡፡
ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኃኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ። መዝሙር 42፡11
ነፍስ ከጥፋት ነፃ የምትወጣው በእውቀት ነው፡፡
ነፍስ በእውቀት ነፃ ካልወጣች በባርነት ትገዛለች፡፡
ነፍስ የተሰራችው በእውቀት እግዚአብሄርን እንድትከተልና
እንድታገለግል ነው፡፡ ነፍስ በእግዚአብሄር
ቃል እውቀት ነፃ ካልወጣች የሰይጣን መጠቀሚያ ትሆናለች፡፡
ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት
ተቀበሉ። ያዕቆብ 1፡21
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እውቀት #ጥበብ #ነፍስ #መዳን #ኢየሱስ #ጌታ
#እግዚአብሔር #እውቀት #መልካም #መታዘዝ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት
#ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #አእምሮ #ሰላም #ማስተዋል #ልጅ
No comments:
Post a Comment