ፈሪሳውያን
ግን ወጥተው እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ተማከሩበት። ኢየሱስም አውቆ ከዚያ ፈቀቅ አለ። ብዙ ሰዎችም ተከተሉት፥ ሁሉንም ፈወሳቸው፥
እንዳይገልጡትም አዘዛቸው፤ በነቢዩ በኢሳይያስ የተባለው
ይፈጸም ዘንድ እንዲህ ሲል፦ እነሆ የመረጥሁት ብላቴናዬ፥ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፥ ፍርድንም ለአሕዛብ ያወራል። አይከራከርም አይጮህምም፥ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም። ፍርድን ድል ለመንሣት እስኪያወጣ፥ የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም የሚጤስን የጥዋፍ ክርም አያጠፋም። ማቴዎስ 11፡14-20
የኢየሱስ
አገልግሎት በሁሉም ነገር ምሳሌ ሊሆንልን የሚችል አገልግሎት ነው፡፡ ኢየሱስ ሲፈውስ ሰዎች ስለሃይማኖታቸው ምክኒያይ ተቃወሙት፡፡
ሲቃወሙት ግን የተቃወሙትን ሰዎች ለማሳመን ሲከራከርና ሲጣላ አይታይም፡፡ ኢየሱስ የተቃወሙትን ሰዎች በክርክር ለመርታትና አፋቸውን
ለማስያዝ ጉልበቱን ሲጨርስ አትመለከቱም፡፡ ኢየሱስ የተቃወሙትን ሰዎች በንግግር ብዛት አፋቸውን ለማስያዝ በዚያም ሃያልነቱን ለማሳየት
ሲከራከር አትመለከቱም፡፡
የኢየሱስ
አገልግሎት ያለው ውስጡ ነው፡፡ የኢየሱስ አገልግሎት ከአንድ ከተወሰነ ቦታ ጋር የተያያዘ አልነበረም፡፡ የኢየሱስ አገልግሎት ከአንደ
የተወሰነ ሁኔታ ጋር የተያያዘም አልነበረም፡፡ የኢየሱስ አገልግሎት ሰዎች ሲቃወሙት አብሮ የሚጠፋ አገልግሎት አልነበረም፡፡ የኢየሱስ አገልግሎት ሰዎች ጎሽ ሲሉት የሚጨምር ሲቃወሙት የሚከስም በውጭው
የአየር ሁኔታ የሚወሰን አገልግሎት አልነበረም፡፡
የኢየሱስ
አገልግሎት ለሌሎች ማሰናከያ የሚሰጥ አገልግሎት አልነበረም፡፡ የኢየሱስ አገልግሎት ደካሞች ሰዎች ሲቃወሙት በድካማቸው ላይ ድካም
የሚጨምርና ይበልጥ የሚያሰናክላቸው አልነበረም፡፡ የኢየሱስ አገልግሎት በተቃውሞ መካከል እንኳን ለሰዎች በጣም የሚጠነቀቅ ነበር፡፡
የኢየሱስ
አገልገሎት ካልታወቅኩ ስሜ ካልገነነ ብሎ ለስሙ ታዋቂነት የሚከራከር ሰው አገልግሎት አልነበረም፡፡ ኢየሱስ ሰዎች ዘጉብኝ አገልግሎቴ
እንዳይወጣ አደረጉት ብሎ ነገሮችን ከሰዎች ጋር የሚያያይዝ አልነበረም፡፡
ኢየሱስ
ስጋት አልነበረበትም፡፡ ኢየሱስ አገልግሎቱ ውስጡ እንዳለ ፣ ውስጡ ያለውን አገልገሎት ሊወስድ የሚችልና አገልግሎቱን ሊያስቆም የሚችል
ማንም ሰው እንደሌለ ያውቃል፡፡
ኢየሱስ
ትኩረቱ ሰዎችን በመጥቀም ፣ ሰዎች ነፃ በማውጣት ፣ ሰዎችን በመፈወስ ላይ እንጂ በስሙ በዝናውና በታዋቂነቱ ላይ አልነበረም፡፡
ኢየሱስ
ጩኸቱ ሳይሰማ ሳይጨበጨብለት በላከው ተማምኖ ድምፁን አጥፍቶ ሰውን ፈውሶ ሰውን ነፃ አውጥቶ የሚያገለግል አገልጋይ ነበር፡፡
ፈሪሳውያን
ግን ወጥተው እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ተማከሩበት። ኢየሱስም አውቆ ከዚያ ፈቀቅ አለ። ብዙ ሰዎችም ተከተሉት፥ ሁሉንም ፈወሳቸው፥
እንዳይገልጡትም አዘዛቸው፤ በነቢዩ በኢሳይያስ የተባለው ይፈጸም ዘንድ እንዲህ ሲል፦ እነሆ የመረጥሁት ብላቴናዬ፥ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት
ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፥ ፍርድንም ለአሕዛብ ያወራል። አይከራከርም አይጮህምም፥ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም።
ፍርድን ድል ለመንሣት እስኪያወጣ፥ የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም የሚጤስን የጥዋፍ ክርም አያጠፋም። ማቴዎስ 11፡14-20
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #አገልግሎት #ሰላም #ክርክር #አይከራከርም #አይጮህምም
#ፈቀቅ #ስኬት # #ስምረት #ፍርድ #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መርካት #ደስታ #ማስተዳደር #እረፍት
No comments:
Post a Comment