Popular Posts

Saturday, February 24, 2018

የቅንነት ልብ

ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ቆሮንቶስ 11፡3
ቅንነት ለሰው ልጅ በጣም አስፈላጊ ሃብት ነው፡፡ ቅንነት የሚቀናበት ባህሪ ነው፡፡ ከእኛ በላይ ቅን የሆኑ ሰዎች ሲያጋጥሙን እንቀናለን፡፡ ቅንነት የሚጓጓለት ባህሪ ነው፡፡ ቅንነት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ለማወቅ እግዚአብሄር ቅንን ሰው እና ጠማማን ሰው እንዴት እንደሚያየው ማየት ወሳኝ ነው፡፡  
ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ፤ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፤ ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፤ ከጠማማም ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ። መዝሙር 18፡25-26
ቅንንት በብዙ የህይወት ተሞክሮ የምንማረው ነገር እንጂ እንደ ስጦታ ከእግዚአብሄር የምንቀበለው አይደለም፡፡ በእግዚአብሄር ነገር እያደግን በሄድን ቁጥር የልባችን መነሻ ሃሳብ እየጠራ ቅንነትን ብቻ እየመረጥን እንሄዳለን፡፡ ጌታን እያገለገልን በሄድን ቁጠር ጌታን የማገልገል አላማችን አንድና እንድ ብቻ ይሆናል፡፡ በጌታ እያደግን በሄድን ቁጥር የምንደብቀው ነገር እየጠፋ ይሄዳል፡፡በጌታ እያደግን በሄድን ቁጥር ህይወታችን ግልፅ እየሆነ ይመጣል፡፡ ጌታን የማገልገላችን ድብቅ አላማ ወደ ብቸኛ አላማ እየጠራ ይሄዳል፡፡
ቅንነት ሁልጊዜ ቅን ላለመሆን እንፈተናለን፡፡ ነገሮች ወደ እኛ ሲመጡ የቀጥተኛና የቅንነት ሃሳብም የጠማማነትና የተንኮል ሃሳብም ወደ እኛ ይመጣሉ፡፡ ታዲያ ሁልጊዜ የቅንንት ሃሳብን መያዝ የጠማማነት ሃሳብን መጣል ይጠበቅብናል፡፡ ይህ ፈተና ደግሞ በህይወታችን ዘመን ሁሉ የሚመጣ ፈተና እንጂ አንዴ ቅን ሆኛለሁ ብለን የምንተወው አይደለም፡፡
ቅን ማለት ቀጥተኛ ማለት ነው፡፡ ቅን ማለት ተንኮል የሌለበት ማለት ነው፡፡ ቅን ማለት በድብቅ ተንኮል የማያስብ ማለት ነው፡፡ ቅን ማለት የሚለውና የሚያስበው አንድ የሆነ ማለት ነው፡፡ ቅን ማለት ጠማምነት የሌለበት ንፁህ ማለት ነው፡፡
የእግዚአብሄር ቃል ግልፅ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል የነጠረ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ንፁህ ነው፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ቅን ነውና ሥራውም ሁሉ በእምነት ነውና። መዝሙር 33፡4
በእግዚአብሄር ቃል ህይወቱ የተለወጠ ሰው ቅንነትን እየጨመረ ይሄዳል፡፡ በእግዚአብሄር ቃል የተነካ ሰው ተንኮልን እየተወ ይሄዳል፡፡ እግዚአብሄርን የሚመስል ሰው ቅን ሰው ነው፡፡ እግዚአብሄርን የምንወክለው ቅን በሆንንበት የህይወታችን ክፍል ብቻ ነው፡፡  
እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፥ ጽድቅንም ይወድዳል፤ ቅንነት ግን ፊቱን ታየዋለች። መዝሙር 117
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#አተረፈ #ንፅህና #ቅንነት #ግልፅ #ንፁህ #ተንኮል #ጠማምነት #ንጉስ #መክሊት #ኢየሱስ #ጌታ #መፅሃፍቅዱስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ስብከት #እምነት

No comments:

Post a Comment