በመጠኑ ኑሩ ንቁም፥ባላጋራችሁ
ዲያብሎስ የሚውጠውን
ፈልጎ እንደሚያጋሳ
አንበሳ ይዞራልና፤1ኛ ጴጥሮስ
5፡8
ላለመሰረቅ መንቃት ይጠይቃል፡፡ ከነቃን የሚያመልጠን
ነገር የለም፡፡ ከነቃን የሚያልፈን ነገር የለም፡፡
ለመንቃት ደግሞ በመጠኑ ለመኖር ይጠይቃል፡፡ በመጠኑ
ሳይኖር መንቃት የማይታሰብ ነው፡፡
አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፥ መከራን
ተቀበል፥ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ፥ አገልግሎትህን ፈጽም። 2ኛ ጢሞቴዎስ 4:5
ከልክ ያለፈ ማንኛውም ጠቃሚ ነገር ጎጂ ነው፡፡
ለመንቃት ሁሉን ነገር በልክ ማድረግ ይጠይቃል፡፡ ከልክ ሲያልፍ ንቃታችንን ላይ ትልቅ ተኝእኖ ያደርጋል፡፡
ምግብ መልካም ነው ምግብ ግን ለሰውነታችን ጉልበትን
ከመስጠት አላማ ሲያልፍና የኑሮ ትምክት ማሳይ ሲሆን ከልክ ያልፋል ይጎዳል፡፡ ልብስ ሰውነትን ለመሸፈን ይረዳል ልብስ ግን የኑሮ
ደረጃችንን ለማሳየት ከተጠቀምንበት ጎጂ ነው፡፡ ሃብትና ንብረት ይጠቅማል ሃብትና ንብረት የእኛን ማንነት እንዲገልፅ በአለም ከንቱ
ውድድር ውስጥ ከገባንበት ግን ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡
ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም
ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ 1ኛ ዮሐንስ
2፡15-16
መጠንን ማወቅ መልካም ነው፡፡ ይህ በቃኝ የምንለው
ነገር መኖር አለበት፡፡ ለመንቃት "ከዚህ በላይ ምን ይሰራልኛል?" የምንለው ነገር መኖር ይኖርበታል፡፡ ለመንቃት
ያለኝ በቂ ነው ማለት ይጠይቃል፡፡ ኑሮዬ ይበቃኛል ካላልን መንቃት የሚባለ ነገር የማይታሰብ ነው፡፡ ካልነቃን ደግሞ የብዙ ነገር
ሰለባ እንሆናለን፡፡
ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን
መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡6
የነቃ ሰው ሌባ እንዲዘርፈው አይፈቅድም፡፡ ለመንቃት
በመጠኑ መኖር ይጠበቅብናል፡፡ ለመንቃት ኑሮዬ ይበቃኛል ማለት ይጠይቃል፡፡ ለመንቃት ነገርን ሁሉ በልክ ማድረግ ይጠይቃል፡፡ ለመንቃት
በአገባብ መመላለስ ይጠይቃል፡፡
ሌሊቱ
አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ። በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤ ሮሜ 13፡12-13
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ
#ፀሎት #ልመና
#ምልጃ #ምስጋና
#ውዳሴ #በመጠኑ
#እንደፈቃዱ #መጠየቅ
#መንበርከክ #ይቃትታል
#መንፈስቅዱስ #እንዲሰማን
#ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም
#አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment