Popular Posts

Tuesday, February 13, 2018

ታላቁ የፍቅር ምሳሌ

ፍቅር እጅግ የከበረ ነገር ነው፡፡ የፍቅር ምሳሌያችን ደግሞ እግዚአብሄር ራሱ ነው፡፡ እግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡  እግዚአብሄር እርሱ ያደረገውን ነገር ነው አድርጉት በፍቅር ኑሩ የሚለን፡፡
የፍቅርን ትርጉም የተረዳነው ከእግዚአብሄር ነው፡፡ ፍቅርን ያወቅነው ከእግዚአብሄር ነው፡፡ የፍቅር ደረጃው እግዚአብሄር ነው፡፡  
እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ 1ኛ ዮሃንስ 3፡16
ካለ እግዚአብሄር ፍቅርን አናውቅም ነበር፡፡ እግዚአብሄርን የማያውቅ ሰው ፍቅርን አያውቅም፡፡ ፍቅር የሌለው ሰው ይመስለዋል እንጂ እግዚአብሄርን አያውቅም፡፡
ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። 1ኛ ዮሃንስ 4፡8
የፍቅር ምርጥ ምሳሌያችን እግዚአብሄር ነው፡፡
እግዚአብሄር እንዲሁ ስለወደደን አንድ ልጁን ሰጠን፡፡ እግዚአብሄር እንዲሁ ስለወደደን ልጁ በመስቀል ላይ እንዲሞትልን ላከው፡፡
ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ሮሜ 5፡8
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ፍቅር #ምንጭ #መውደድ #ስሜት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ትዕግስት #መንፈስቅዱስ #ማስተዋል #ልብ #መሪ  

No comments:

Post a Comment