Popular Posts

Thursday, February 15, 2018

ፈጣሪሽ ባልሽ ነው

ፈጣሪሽ ባልሽ ነው፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ የእስራኤልም ቅዱስ ታዲጊሽ ነው፥ እርሱም የምድር ሁሉ አምላክ ይባላል። ኢሳያስ 54፡5
እግዚአብሄር አምላክ በብዙ ቦታዎች እንደ ህዝቡ ባል ተመስሏል፡፡ ፈጣሪሽ ባልሽ ነው ማለት ፈጣሪሽ ባልሽ ሊያደርግልሽ የሚችለውን ነገሮች መምራት ፣ መጠበቅ ፣ መንከባከብና ማፅናናት ሊያደርግልሽ ይችላል ማለት ነው፡፡
ሰዎች የምድር ባል ሊደርስባቸው የማይችሉ ብዙ ፍላጎቶች አሏቸው፡፡  እንዲያውም ዋና ዋናውን የሰው ልጅ ፍላጎት ሊያሟላ የሚችለው እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ እውነት ነው ባል ሊያሟላ የሚችላቸው ጥቂት ነገሮች አሉ፡፡ ነገር ግን ሊያሟላ የማይችላቸው ብዙ ነገሮች ደግሞ አሉ፡፡
ስለዚህ ነው የምድር ባልዋን ልጅ ስጠኝ ብላ ስታስቸግረው እኔ ልጅን በሚሰጥ በእግዚአብሄር ቦታ ነኝን ብሎ ያቆብ የመለሰው፡፡
ራሔልም ለያዕቆብ ልጆችን እንዳልወለደች ባየች ጊዜ በእኅትዋ ቀናችባት፤ ያቆብንም፦ ልጅ ስጠኝ፤ ይህስ ካልሆነ እሞታለሁ አለችው። ያዕቆብም ራሔልን ተቆጥቶ፦ በውኑ እኔ የሆድን ፍሬ በነሣሽ በእግዚአብሔር ቦታ ነኝን? አላት። ዘፍጥረት 30፡1-2
አንዳንዴ ሚስቶች ከባሎች የሚጠብቁት ነገር ከፈጣሪ ባላቸው ከእግዚአብሄር ብቻ የሚያገኙትን ነገር ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሚስቶች በባላቸው የሚሰናከሉት ፈጣሪ ባላቸው ብቻ ሊያደርግላቸው የሚችለውን ነገር ከምድር ባላቸው ሲጠብቁ ነው፡፡ ባልሽ መልካምን የሚያደርገው ፈጣሪሽ ባልሽ እግዚአብሄር ሲጠቀምበት ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር ካልተጠቀመበት በራሱ በጎነት የለውም፡፡
እግዚአብሔርን፦ አንተ ጌታዬ ነህ አልሁ፤ ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም። መዝሙር 16፡2
በእግዚአብሄር የረካ ሰው ይረካል፡፡ በእግዚአብሄር የረካች ሴት በባልዋ ትረካለች፡፡ በእግዚአብሄር የረካች ሴት በባልዋም ባትረካ እንኳን በእግዚአብሄር መሪነት ፣ ጥበቃ ፣ እንክብካቤና ማፅናናት ትረካለች፡፡ ባል የማይረስበት እግዚአብሄር ብቻ የሚደርስበት ብዙ ፍላጎት አለ፡፡ ባልዋ ባላረካት ነገር ላይ አይኖችዋን ወደ ፈጣሪ ባልዋ ማንሳትዋ ህይወትዋን ሙሉ ያደርገዋል፡፡
ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ ያገቡ በባላቸው ወይም በሚስታቸው ላይ ከመጠን በላይ እንዳይደገፉ የሚያዘው፡፡
ዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ 1ኛ ቆሮንቶስ 7፡29
ፈጣሪሽ ባልሽ ነው፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ የእስራኤልም ቅዱስ ታዲጊሽ ነው፥ እርሱም የምድር ሁሉ አምላክ ይባላል። ኢሳያስ 54፡5
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ያገባ #ያላገባ #ኣላፊ  #ፈጣሪ #ባልሽ # #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment