ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው፥ ዕብራውያን 9፡27
እግዚአብሄር ለብዙ ሰዎች መለወጥ ምክኒያት ያደረጋቸው ወንጌላዊው ቢሊ ግርሃም ወደ ጌታ እንደ ሄዱ ዛሬ ከወደ አሜሪካ ምድር አንድ ዜና ሰማን፡፡
ቢሊ ግርሃም በዘላለም ህይወት ሊነቁ ከምድር አንቀላፍተዋል፡፡ ዛሬ ህይወታቸው በጌታ የነበራቸው ጉዞ የሚበሰርበት የጊዜ ነው፡፡
ነገር ግን በዚህ አጋጣሚ ስለሊግርሃም የሰማሁትን አንድ ታሪክ ላካፍላችሁ፡፡
ቢሊግርሃም በተነሱ ጊዜ የተነሱ እንደ እርሳቸው የተቀቡ ሁለት ወንጌላዊያን ነበሩ፡፡ ሁለቱ ወንጌላዊያን እንደ ቢሊ ግርሃም በሃይል ወንጌልን የሚያገለግሉ አገልጋዮች ነበሩ፡፡ ሁለቱ ወንጌላዊያን እንደ ቢሊ ግርሃም ብዙ ሰዎች ጌታን እንዲያገኙ የረዱ ወንጌላዊያን ነበሩ፡፡ ሁለቱ ወንጌላዊያን ከቢሊግርሃም ያላነሰ እግዚአብሄር በሃይል የሚጠቀምባቸው ነበሩ፡፡
ነገር ግን ጥቂት ብቻ ታይተው የጠፉ ወንጌላዊያን ነበሩ፡፡ የቢሊ ግርሃም አገልግሎት ሲቀጥል የእነርሱ አገልግሎት ግን የተቀጨው በአጭሩ ነበር ፡፡
ታዲያ ቢሊ ግርሃምንና ሁለቱን ወንጌላዊያን የለያቸው ታማኝነት ነበር፡፡ ቢሊ ግርሃም እግዚአብሄር የሰጣቸውን አገልግሎት በጥንቃቄና በታማኝነት ይይዙ ነበር፡፡ ቢሊግርሃም እግዚአብሄር የሰጣቸውን ተሰሚነት ለራሳቸው የግል ጥቅም ላለመጠቅም ይጠነቀቁ ነበር፡፡ ቢሊ ግርሃም በአገልግሎት የሚመጣውን ገንዘብ ግልፅነትና ተጠያቂነት በተሞላበት መልኩ እንዲያዝ ቶሎ ለባለሙያ ይሰጡ ነበር፡፡ ቢሊ ግርሃም እግዚአብሄር ተሰሚነትን በሰጣቸው መጠን ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉ የሚማር ልብ የነበራቸው ነበሩ፡፡ ቢሊ ግርሃም እግዚአብሄር ተሰሚነትን በሰጣቸው ቁጥር ለመማር ለመለወጥ በትጋት ይሰሩ ነበር፡፡ የሚማር ልብ ስለ ነበራቸው ነው በብዙ ዘመናት መካከል ተፈላጊነታቸው እየጨመረ የሄደው፡፡
ቢሊ ግርሃም እግዚአብሄር የሰጣቸውን የአገልግሎት ፀጋ ጠብቀው የሚያቆዩበትና በዘመናት መካከል ልብዙዎች በረከትና ጥቅም የሚያውሉበት ባህሪ ነበራቸው፡፡ ቢሊግርሃም በአገልግሎት ብቻ ሳይሆን ክርስትያናዊ ባህሪያቸውን ለመስራት በትጋት ይሰሩ ነበር፡፡
ቢሊግርሃም እግዚአብሄር ተሰሚነትን በሰጣቸው ቁጥር ከእግዚአብሄር ቃል ላለመውጣት ራሳቸውን ትሁት ያደርጉ ነበር፡፡ እግዚአብሄር በተከፈተላቸው በር ሁሉ ኢየሱስና እርሱም እንደተሰቀለ ቀላል የሆነውን መልእክት ነበር ከፕሬዝዳንቶች እስከ ተራ ሰው ያስተላልፉ ነበር፡፡
ወንድሞች ሆይ፥ ስለ አንዱ በአንዱ ላይ አንዳችሁም እንዳይታበዩ፦ ከተጻፈው አትለፍ የሚለውን በእኛ ትማሩ ዘንድ፥ ይህን በእናንተ ምክንያት ስለ ራሴና ስለ አጵሎስ እንደ ምሳሌ ተናገርሁ። 1ኛ ቆሮንቶስ 4፡6
ቢሊግርሃም አገልግሎታቸው በንፅህና ዘመናትን ስለ ዘለቀ አምስት ያህል የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶችን ያማክሩ እንደነበርና ለ11 የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ስለጌታ አዳኝነት እንደተናገሩ ይነገርላቸዋል፡፡
መፅሃፍ ቅዱስ የሽማግሌዎችም ጌጥ ሽበት ነው እንደሚል ቢሊ ግርሃም የእግዚአብሄርን ሃሳብ በዘመናቸው አገልግለው እደሜ ጠግበው ወደጌታ ሄደዋል፡፡
እያንዳንዳችንም በተሰጠን በዚህ ቀን በዘመናችን የእግዚአብሄርን ስራ ሰርተን እንለፍ፡፡
ዳዊትም በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን አሳብ ካገለገለ በኋላ አንቀላፋ፥ ከአባቶቹም ጋር ተጨምሮ መበስበስን አየ፤ ሐዋርያት 13፡36
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #አገልግሎት #ወንጌል #ታማኝነት #ትጋት #ስጦታ #ማንቀላፋት #ቢሊግርሃም #ቢሊግራም #በረከት #ስኬት #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መርካት #ደስታ #ማስተዳደር #እረፍት
No comments:
Post a Comment