Popular Posts

Follow by Email

Thursday, February 15, 2018

የማንጠቅም ባሪያዎች ነን

ከእናንተም የሚያርስ ወይም ከብትን የሚጠብቅ ባሪያ ያለው፥ ከእርሻ ሲመለስ፦ ወዲያው ቅረብና በማዕድ ተቀመጥ የሚለው ማን ነው? የምበላውን እራቴን አሰናዳልኝ፥ እስክበላና እስክጠጣ ድረስ ታጥቀህ አገልግለኝ፥ በኋላም አንተ ብላና ጠጣ የሚለው አይደለምን? ያንን ባሪያ ያዘዘውን ስላደረገ ያመሰግነዋልን? እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፦ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ። ሉቃስ 17፡7-10
ምንም መልካም ነገር ቢኖረን የራሳችን አይደለም፡፡ ምንም መልካም ነገር ቢኖረን ከእግዚአብሄር የተቀበልነው ነው፡፡ መጀመሪያውኑም የራሳችን እንደሆነ እንዳልተቀበልነው ማሰብ የለብንም፡፡
በልብህም፦ ጉልበቴ የእጄም ብርታት ይህን ሀብት አመጣልኝ እንዳትል። ነገር ግን ዛሬ እንደ ሆነ ለአባቶችህ የማለውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ፥ ሀብት ለማከማቸት እርሱ ጉልበት ሰጥቶሃልና አምላክህን እግዚአብሔርን አስብ። ዘዳግም 8፡17-18
ሰው የሚከናወንለት ስለሰራ ብቻ አይደለም፡፡ ሰርተህም እግዚአብሄር የሰራኸውን ወደ ክንውን ሊያመጣልህ ያስፈልጋል፡፡
የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፤ ነህምያ 2፡20
በምንም ሁኔታ የምንበልጥበት ነገር ካልን እንድንበልጥ ያደረገን እግዚአብሄር ነው፡፡ ምንም የበለጥንበት ነገር ካለ ከእግዚአብሄር የተቀበልነው እንጂ የራሳችን አይደለም፡፡
አንተ እንድትበልጥ ማን አድርጎሃል? ያልተቀበልኸውስ ምን አለህ? የተቀበልህ ከሆንህ ግን እንዳልተቀበልህ የምትመካ ስለ ምንድር ነው? 1ኛ ቆሮንቶስ 4፡7
ከእግዚአብሄር ውጭ በጎነት የለንም፡፡ እግዚአብሄር ካልተጠቀመብን ለምንም አንጠቅምም፡፡ ጠቃሚ የሆነው እግዚአብሄር ስለተጠቀመብን ብቻ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር ውጭ ለምንም አንሆንም፡፡
እግዚአብሔርን፦ አንተ ጌታዬ ነህ አልሁ፤ ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም። መዝሙር 16፡2
እግዚአብሄር ስለተጠቀመብን እንጂ ህይወታቸውን ያባክናሉ ከምንላቸው በአካባቢያችን ካሉት ሰዎች በምን እንበልጣለን? የእግዚአብሄር ፀጋ በህይወታችን ስለሰራ እንጂ ከሌላው በምን እንለያለን? በምንም የተለየን ከሆንን በራሳችን አይደለም በፀጋው ነው፡፡  
ስለዚህ እግዚአብሄርን ካገለገልን በኋላ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን ማለት እንጂ መመካት አያስፈልግም፡፡ ላስቻለንና እግዚአብሄርና ለበጎነታችን ምንጭ እውቅና በመስጠትና እርሱን በማክበር እኛ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን ማለት ትክክለኛ የልብ ዝንባሌ ነው፡፡
እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፦ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ። ሉቃስ 17፡10
እንደዚህ አይነት የትህትና የልብ ዝንባሌ ያለው ሰው የእግዚአብሄር ሃይል አይቋረጥበትም፡፡ ትሁት የሆነ ሰው ስለበጎነቱ ለራሱ ክብሩን የማይወስድ ነገር ግን ሁል ጊዜ ለእግዚአብሄር ክብርን የሚሰጥ ሰው በአገልግሎት ይዘልቃል፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ትህትና #መዋረድ #ባህሪ #ዝቅታ ትህትና #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment