Popular Posts

Thursday, February 8, 2018

ራሳችንን እናማጥናለን

ጌታን የምናገለግለው በሚታይ ነገር ስለደላንና ሁሉ ነገር አልጋ በአልጋ ስለሆነልን አይደለም፡፡ ጌታን የምናገለግለው ጌታን ማገልገል ስላለብን ነው፡፡ ጌታን የምናገለግለው የምንፈልገው ነገር ሁሉ ተሟልቶልን አይደለም፡፡ ጌታን የምናገለግለው ጉድለታችን በእግዚአብሄር ፀጋ እየተሸፈነ ነው፡፡
ጌታን የምናገለግለው የተሻለ የሙያ መስክ ስለሆነ አይደለም፡፡ ጌታን የምናገለገልው በእግዚአብሄር ስለተጠራን ነው፡፡ ጌታን የምናገለግለው ከዚህ የተሻለ የምንሰራው ስራ ስለሌለ አይደለም፡፡ ጌታን የምናገለግልው በህይወታችን ያለውን የእግዚአብሄርን ሃሳብ ለመፈፀም ነው፡፡
ጌታን የምናገለግለው ከግል ጥቅም አንፃር አትራፊ ስራ ስለሆነ አይደለም፡፡ ጌታን የምናገለግለው እግዚአብሄር ለዚህ አገልግሎት እንደፈጠረን ስለምናምን ነው፡፡ ጌታን የምናገለግለው መብቱና ስልጣኑ ብዙ ስለሆነ አይደለም፡፡ ጌታን የምናገለግለው መብታችንንና ጥቅማችንን እየተውን ነው፡፡
ሌሎች በእናንተ ላይ ይህን መብት የሚካፈሉ ከሆኑ እኛማ ይልቁን እንዴታ? ነገር ግን የክርስቶስን ወንጌል እንዳንከለክል በሁሉ እንታገሣለን እንጂ በዚህ መብት አልተጠቀምንም። 1ኛ ቆሮንቶስ 9፡12
እግዚአብሄርን የምናገለግለው ሁሉ ሰው ተቀብሎን አይደለም፡፡ እግዚአብሄርን የምናገለግለው እግዚአብሄር ስለላከን ነው፡፡ እግዚአብሄርን የምናገለግልው የምናገለግላቸው ሁልጊዜ እያስደሰቱን አይደለም፡፡ እግዚአብሄርን የምናገለግልው በጌታ ደስ በመሰኘት ብቻ ነው፡፡
ለዋኖቻችሁ ታዘዙና ተገዙ፤ እነርሱ ስሌትን እንደሚሰጡ አድርገው፥ ይህንኑ በደስታ እንጂ በኃዘን እንዳያደርጉት፥ ይህ የማይጠቅማችሁ ነበርና፥ ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ። ዕብራውያን 13፡17
ስለዚህ የተሻለ ስለሚከፈለው ነው ይህ ደሞዝ አንድ ቀን ሲቆም አገልግሎት ያቆማል ለሚሉት መሰናከያ መሆን አንፈልግም፡፡ ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ቢከፈለንም ባይከፈለንም እናገለግላለን፡፡ ቢመቸንም ባይመቸንም እናገለግላለን፡፡ በጊዜውም አለጊዜውም እንፀናለን፡፡
እኔ ግን ከእነዚህ ሁሉ ምንም አልተጠቀምሁም። እንዲህ እንዲሆንልኝ ይህን አልጽፍም፤ ማንም ትምክህቴን ከንቱ ከሚያደርግብኝ ሞት ይሻለኛልና። 1ኛ ቆሮንቶስ 9፡15
ስለዚህ በከፍታና በዝቅታ ራሳችንን እናማጥናለን፡፡ ከሰው ምንም ሳንጠብቅ እግዚአብሄርን ማገልገል ትምክታችን ነው፡፡ እግዚአብሄርን በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ማገልገላችን ሃብታችን ትምክታችን ነው፡፡ ትምክታችንን ማንም ከንቱ ከሚያደርግብን ሞት ይሻለናል፡፡
አገልግሎታችንም እንዳይነቀፍ በአንዳች ነገር ማሰናከያ ከቶ አንሰጥም። ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፤ በብዙ መጽናት፥ በመከራ፥ በችግር፥ በጭንቀት፥ በመገረፍ፥ በወኅኒ፥ በሁከት፥ በድካም፥ እንቅልፍ በማጣት፥ በመጦም፥ በንጽህና፥ በእውቀት፥ በትዕግሥት፥ በቸርነት፥ በመንፈስ ቅዱስ፥ ግብዝነት በሌለው ፍቅር፥ በእውነት ቃል፥ በእግዚአብሔር ኃይል፥ ለቀኝና ለግራ በሚሆን በጽድቅ የጦር ዕቃ፥ በክብርና በውርደት፥ በክፉ ወሬና በመልካም ወሬ ራሳችንን እናማጥናለን፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡3-8
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #ፀጋ #የሚያስችልሃይል #እውቀት #ምስጋና #ትህትና #ልብ #እምነት #ፀሎት #ማማጠን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment