እግዚአብሔር በአንድ መንገድ በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም። መጽሐፈ ኢዮብ 33፡14
እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው ለህብረት ነው፡፡
እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው እርሱ ሲናገር በትክክል እንዲሰማው አድርጎ በመልኩና በአምሳሉ ነው፡፡ ሰው እግዚአብሔርን መስማት ከሚፈልገው
በላይ እግዚአብሔር ለሰው መናገር ይወዳል፡፡ ሰው እግዚአብሔርን ለመስማት ከሚፈልገው በላይ እግዚአብሔር በሰው መሰማት ይፈልጋል፡፡
የሰው እግዚአብሔርን ያለመስማት ችግሩ ሰው ብቻ ነው፡፡
እግዚአብሔር ሰው እንዲሰማው እና እንዲረዳው ይፈልጋል፡፡
እግዚአብሔር
በምድር ላይ አላማውን ለመፈፀም ሰውን ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር በሰው እንዲሰማ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር ይናገራል፡፡ ሰው እኔ
አልሰማሁትም ማለት ይችላል እንጂ እግዚአብሔር አልተናገረኝም ማለት አይችልም፡፡
እግዚአብሔርም
እንዲሁ ያልተናገረንን እንድናደርገው አይጠብቅብንም፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
No comments:
Post a Comment