Popular Posts

Thursday, June 1, 2023

እግዚአብሔርን እንዲሰማው የተፈጠረው ሰው

 


እግዚአብሔርን ሳይሰሙ እውነተኛውን የእግዚአብሔርን ህይወት እኖራለሁ ማለት ዘበት ነው፡፡ የሃይማኖትን መልክ መያዝ ይችላል ነገር ግን ካለ እግዚአብሔር ድምፅ እውነተኛ መንፈሳዊነት መከተል አይቻልም፡፡

እግዚአብሔርን ለመከተል እግዚአብሔርን መስማት እና መረዳት ይጠይቃል፡፡ እግዚአብሔርን ሳንሰማ ፍቃዱን እንፈፅማለን ማለት የማይሆን ነገር ነው፡፡

ሰው የተፈጠረው እግዚአብሔርን እንዲሰማ ነው፡፡

እግዚአብሔርን የመስማት ሃሳብ ከጊዜ በኋላ በሰው የተፈጠረ ሃሳብ አይደለም፡፡ ሰው የተፈጠረው እግዚአብሔርን እንዲሰማ እንደነበረ ከጥንት አፈጣጠሩ በቀላሉ እንረዳለን፡፡

ሰው የተፈጠረው በምድር ላይ የእግዚአብሔርን አላማ እንዲያስፈፅም ነው፡፡ ሃሳቡን እንዲያስፈፅምለት እና እንደ ራሱ አድርጎ ምድርን እንዲያስተዳደርለት እግዚአብሔር ሰውን በመልኩ እና በአምሳሉ ፈጠረው፡፡ ሰው በእግዚአብሔር መልክ የተፈጠረው እርሱን እየሰማ ምድርን እርሱ ራሱ እንደሚፈልገው እንዲያስተዳደር ነበር፡፡

ሰው በመጀመሪያ በእግዚአብሔር መልክ እና አምሳል የተፈጠረው እግዚአብሔርን እንዲሰማ ተደርጎ ነው፡፡ ሰው እግዚእብሄርን ሳይሰማ የእርሱ ወኪል ሊሆን እንደማይችል እግዚአብሔርን አውቆ ሰውን በመልኩ እና በአምሳሉ ፈጠረው፡፡

በእግዚአብሔር መልክና አምሳል የተፈጠረው ሰውበሚገባ እግዚአብሔርን መስማት እና መረዳት እንዲችል ነበር፡፡

እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። ኦሪት ዘፍጥረት 1፡26-27

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa


No comments:

Post a Comment