Popular Posts

Sunday, January 14, 2024

ያልተጋባች ሴትና ድንግል

  


ያልተጋባች ሴትና ድንግል 


1 ቆሮንጦስ 7:34 ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ፤የተጋባች ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንድታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች።

ጋብቻ ክቡር ነው:: ለሁሉም ሰው ግን አይደለም:: 

ጋብቻ ክቡር ነው ግዴታ ግን አይደለም:: ያገባ በህይወቱ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሊፈፅም እንደሚችልሁሉ ያላገባ የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈፀም ይችላልየእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈፀምንበተመለከተ ባገባና ባላገባ መካከል ልዩነት የለም:: 

እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት እንደዚሁ ይኑር። 1 ቆሮንጦስ 7:20

ያላገባ የእግዚአብሔርን አላማ ሊስት ይችላል:: ያገባ እግዚአብሔር በህይወቱ ያስቀመጠውን አላማተከትሎ እግዚአብሔርን ሊያከብር ይችላል:: 

የሰው ታማኝነት በማግባት እና ባለማግባት አይመዘንም::

እንዲያውም ካገባ ይልቅ ያላገባ አሳቡ ሳይከፋፈል እግዚአብሔርን ሊያገለግልበት  የሚችልበት ሰፊእድል አለው:: 

አንዳንድ ሰዎችን አሳባቸው በባል ወይም በሚስት እንዳይከፋፈል የሚፈልጋቸው ሰዎች አሉ:: 

እግዚአብሔር ለራሱ ብቻ አገልጋይ እንዲሆኑ የሚቀናባቸው ሰዎች አሉ:: 

1 ቆሮንጦስ 7:34 ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ፤የተጋባች ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንድታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች።


አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa


#ያገባ #ያላገባ #አላፊ #ኢየሱስ #ጌታ #ጋብቻ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ሚስት #መዳን#መፅሃፍቅዱስ #ባል #እምነት #ወንድ #ፍቅር #ትዳር #ሰላም #ሴት #አቢይ #አቢይዋቁማ#አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment