Popular Posts

Follow by Email

Friday, June 16, 2017

የዘላለም አባት

እግዚአብሄር - አባት የሁልጊዜ ነው፡፡
አባት ስሜቱን ዋጥ ያደርጋል፡፡ አባት ተለዋዋጭ ስሜቱን አይከተልም፡፡ አባት በመርህ ይመራል፡፡   
ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። ኢሳይያስ 9፡6
እግዚአብሄር - አባት ሰብሳቢ ነው፡፡
አባት ፍቅር አለው፡፡ አባት ለመሰብሰብ እርምጃ ይወስዳል፡፡ አባት የማይሰራ /passive/ ዝም ብሎ የሚጠብቅ አይደለም፡፡ አባት ሁኔታውን ለመለወጥ ይሄዳል እርምጃ ይወስዳል፡፡  
ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም። ማቴዎስ 23፥37
እግዚአብሄር - አባት አይፎካከርም ይራራል
አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል፤ መዝሙር 103፡13
እግዚአብሄር - አባት ያፅናናል
የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። 2ኛ ቆሮንቶስ 1፡3
እግዚአብሄር - አባት ይጋፈጣል
እውነተኛ አባት በቤተሰብ የሚነሱ ጉዳዮችን ይጋፈጣል፡፡ እውነተኛ አባት የአባትነት ሃላፊነቱን ይወጣል፡፡
እግዚአብሄር - አባት ይሸከማል
ወደዚህም ስፋራ እስክትመጡ ድረስ በሄዳችሁበት መንገድ ሁሉ፥ ሰው ልጁን እንዲሸከም አምላክህ እግዚአብሔር እንደተሸከመህ አንተ አይተሃል። ዘዳግም 1፡31
እግዚአብሄር - አባት ግድ ይለዋል
ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፥ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን? ማቴዎስ 6፡26
እናንተም የምትበሉትን የምትጠጡትንም አትፈልጉ፥ አታወላውሉም፤ ይህንስ ሁሉ በዓለም ያሉ አሕዛብ ይፈልጉታልና፤ የእናንተም አባት ይህ እንዲያስፈልጋችሁ ያውቃል። ሉቃስ 12፡29-30
እግዚአብሄር - አባት ይታገሳል
እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? ሉቃስ 18፡7

እግዚአብሄር - አባት ይሰጣል
እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ፥ በሰማይ ያለው አባት ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መንፈስ ቅዱስን ይሰጣቸው? ሉቃስ 11፡13
እግዚአብሄር - አባት ይመክራል ይገስፃል ይቀጣል
እንደ ልጆችም ከእናንተ ጋር፦ ልጄ ሆይ፥ የጌታን ቅጣት አታቅልል፥ በሚገሥጽህም ጊዜ አትድከም፤ ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና፥ የሚቀበለውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል ብሎ የሚነጋገረውን ምክር ረስታችኋል። ዕብራውያን 12፡5-6
እግዚአብሄር - አባት እውቅና ይሰጣል ያበረታታል
እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ። ማቴዎስ 4፡17
እግዚአብሄር - አባት ያምናል
ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረኝ፥ ኃይል የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡12
እግዚአብሄር -አባት ግንኙነትን ያበረታታል
አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና። የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል። ሮሜ 8፡15-16
እግዚአብሄር - አባት ይጠነቀቃል ራሱን ይገዛል
አባቶች ሆይ፥ ልባቸው እንዳይዝል ልጆቻችሁን አታበሳጩአቸው። ቆላስይስ 3፡21
ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል። 1ኛ ቆሮንቶስ 10፡13
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ወላጅ #ፍቅር #አባት #እርማት #ጥንካሬ #አቅርቦት #አባትነት #ተግሳፅ  #መሪ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment