በአንድ አካልም የተጠራችሁለት ደግሞ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ፤ ወደ ቆላስይስ
ሰዎች 3፡15
ክርስቶስ ኢየሱስን እንደአዳኝ አምነን ከተቀበልንበት ቅፅበት ጀምሮ ክርስቶስ በልባችን
ይኖራል፡፡ በውስጣችን ያለው የክርስቶስ ሰላም ምን ማድረግ እንዳለብን ይመራናል፡፡
አእምሮዋችን ቢጨነቅም እንኳን በልባችን ሰላም ከተሰማን ልናደርገው ያሰብነው ነገር የእግዚአብሄር
ፈቃድ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ነገር ግን አንድን ነገር ለማድረግ ስናስብ ልባችን የሚረበሽ እና የውስጥ ሰላማችንን የምናጣ ከሆንን
ያ ነገር ለእኛ የእግዚአብሄር ፈቃድ እንዳልሆነ እናውቃለን፡፡
የአእምሮዋችንን አስተሳሰብ ሰምተን የእግዚአብሄርን ፈቃድ ልንስተው ልንሳሳት እንችላለን፡፡
ነገር ግን በልባችን ያለውን ሰላም ሰምተን እና ተከትለን ልንሳሳት አንችልም፡፡ ለአእምሮዋችንም ባይገባውም በልባችን ያለውን ሰላም
በመከተል ብቻ የእግዚአብሄርን ፈቃድ መከተል አንችላለን፡፡ በልባችን ሰላም ከተሰማን እና ልባችን የማይፈርድብን ከሆነ ሰላም ከሆነ
የእግዚአብሄር ፈቃድ መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡
መፅሃፍ ቅዱስ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ የሚለው ሰላምን እንደመሪ እንድንሰማው
እና እንድንከተለው ነው፡፡
በአንድ አካልም የተጠራችሁለት ደግሞ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ፤ ወደ ቆላስይስ
ሰዎች 3፡15
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
No comments:
Post a Comment