Popular Posts

Thursday, July 26, 2018

መልስ የሌለው ፈተና

ፈተና ለእኛ መልስ የሌለው ጥያቄ ነው፡፡ በህይወት መልስ የሌለው ጥያቄ የለም፡፡ በህይወት መውጫ የሌለው ፈተና የለም፡፡ ፈተና የለም ማለት ስህተት እንደሆነ ሁሉ ፈተናው መልስ የለውም ማለት እንዲሁ ስህተት ነው፡፡ ፈተና ፈተና የሚሆነው መውጫው ሲታጣ ነው፡፡ ፈተና ፈተና የሚሆነው መውጫውን ስለማናየው ነው፡፡
እግዚአብሄር ካለንበት ፈተና መውጣት እንደምንችል ያውቃል፡፡ በእኛ በኩል የፈተናችን መውጫ አይታይም፡፡ በእግዚአብሄር በኩል ግን የፈተናችን መውጫ ይታያል፡፡ ፈተና ከእኛ እንጂ ከእግዚአብሄር ቁጥጥር ውጭ አይደለም፡፡ በእኛ ላይ የሚደርሰው ፈተና እግዚአብሄር የፈቀደለት ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር ያልፈቀደው ፈተና በእኛ ላይ አይደርስም፡፡ እግዚአብሄር ከምንችለው በላይ እንዳንፈተን የማይፈቅደው ስለዚህ ነው፡፡  
ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10፡13
ፈተና ፈተና የሚሆነው መፍትሄው ለእኛ ስለማይታየን ነው፡፡ ፈተና የሚገድለን የሚጥለን የሚያዋርደን ይመስለናል፡፡ የማያስቸኩል እና የማያጣድፍ እንዳንታገስ የማይፈትን ፈተና ፈተና አይደለም፡፡ የፈተናን መፍትሄ የምናይበት ብቸኛው ቦታ ከእግዚአብሄር ነው፡፡ ይዘግይ ይፍጠንም የፈተናው መልስ ይመጣል፡፡ ፈተናውን እንድንታገሰው የእግዚአብሄር እርዳታ ያስፈልገናል፡፡ ካለ እግዚአብሄር እርዳታ ፈተናን መታገስ አንችልም፡፡  
ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10፡13
ከፈተና ጊዜ በላይ የእግዚአብሄር ፀጋ የሚያስፈልግን ጊዜ የለም፡፡ ካለ እግዚአብሄር ፀጋ ፈተናን ማለፍ አንችልም፡፡ ፈተና ፈተና የሚሆነው መውጫው ከአቅማችን በላይ ስለሆነ ነው፡፡ ፈተናን ማለፍ የምንችለው በእግዚአብሄር ፀጋ ብቻ ነው፡፡ ፈተናን ማለፍ የምንችለው በእግዚአብሄር እርዳታ ብቻ ነው፡፡
እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ። ወደ ዕብራውያን 4፡16
የትኛውም ፈተና ከአቅም በላየ የሚሆነው ለእኛ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር ከአቅም በላይ የሆነ ፈተና የለም፡፡ በእግዚአብሄር እርዳታ የማንወጣው ተራራ የለም፡፡ በእግዚአብሄር ጥበብ የማንፈታው ቋጠሮ የለም፡፡ በእግዚአብሄር ማፅናናት የማንወጣው ሃዘን የለም፡፡ በእግዚአብሄር ፀጋ የማንደርስበት ፍጥነት የለም፡፡ በእግዚአብሄር እርዳታ የማንታገሰው ጊዜ የለም፡፡ ለማንኛውም ፈተናና ችግር መፍትሄ የሆነ ፀጋ በእግዚአብሄር ዘንድ አለ፡፡ ብዙ ጊዜ ይመስለናል እንጂ የእግዚአብሄር ፀጋ የማይፈታው ተግዳሮት ከዚህ በፊትም አልነበረም ከዚህም በኋላ አይኖርም፡
እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ። ወደ ዕብራውያን 4፡16
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #ፀጋ #የሚያስችልሃይል #የሚረዳንን #ፀሎት #እውቀት #ምስጋና #ትህትና #ልብ #እምነት #ፀሎት #ማማጠን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment