Popular Posts

Sunday, January 7, 2024

ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ! ክፍል 2

 

ዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7፡29

እግዚአብሄር በትዳር ውስጥ ካስቀመጠው በረከት አንፃር ባል ከሚስቱ የሚጠቀመው ነገር አለ ሚስትም ከባልዋ የምትጠቀመው ነገር አለ፡፡

የዚህ ጥቅስ ትእዛዝ ባል ከሚስቱ ሚስትም ከባልዋ አትጠቀም የሚል ማስጠንቀቂያ አይደለም፡፡ የዚህ ትእዛዝ አላማው ባል ከሚስቱ በሚጠቀመው ጥቅም ላይ ከመጠን ያለፈ እንዳይደገፍ እንዲጠነቀቅ ብቻ ነው፡፡ እንዲሁም ደግሞ ሚስት ከባልዋ በምትጠቀመው ጥቅም ላይ ከመጠን ያለፈ እንዳትደገፍ እና እንድትጠነቀቅ ብቻ ነው፡፡

ምንም አይነት መልካም ነገር ከመጠን ሲያልፍ መጀመሪያ የተፈጠረበትን አላማውን ይስታል፡፡ ምንም መልካም ነገር ከመጠን ሲያልፍ ይጎዳል፡፡

ባል በሚስቱ ላይ ያለው ከመጠን ያለፈ መደገፍ የትዳርን አላማ ያስተዋል፡፡ ሚስት በባልዋ ላይ ያላት ከመጠን ያለፈ መደገፍ በትዳሩ ውስጥ እግዚአብሄር ያዘጋጀውን በረከት በሙሉ ተጠቃሚ እንዳትሆን እንቅፋት ይሆንባታል፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ያገባ #ያላገባ #አላፊ #ኢየሱስ #ጌታ #ጋብቻ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ሚስት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ባል #እምነት #ወንድ #ፍቅር #ትዳር #ሰላም #ሴት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ


No comments:

Post a Comment