Popular Posts

Friday, June 15, 2018

ፍቅር ከልካይ የለውም

የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው። እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም። ገላትያ 5፡22-23
ፍቅር ስለሌላው መልካም ማሰብ ፣ መልካም መናገርና መልካም ማድረግ ነው፡፡
ፍቅር በመረዳት ከሌላው ጋር ራስን ማስተባበር ነው፡፡
ፍቅር የህግ ፍፃሜ ነው፡፡ ፍቅር ህግን ሁሉ ይፈፅማል፡፡ ፍቅር ህግን ሁሉ የሚፈፅም የህግ ፍፃሜ በመሆኑ በፍቅር ላይ የሚሰራ ምንም ህግ የለም፡፡ ህግ በፍቅር ላይ አቅም ያጣል፡፡ ህግ በፍቅር ላይ አቃቂር ማውጣት አይችልም፡፡ ህግ በፍቅር ላይ ነቀፋ ሊያገኝበት አይችልም፡፡
እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም ዕዳ አይኑርባችሁ፥ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታልና። አታመንዝር፥ አትግደል፥ አትስረቅ፥ በውሸት አትመስክር፥ አትመኝ የሚለው ከሌላይቱ ትእዛዝ ሁሉ ጋር በዚህ፦ ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ በሚለው ቃል ተጠቅልሎአል። ፍቅር ለባልንጀራው ክፉ አያደርግም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 13፡8-10
ፍቅር ንፁህ ነው
ፍቅር ንፁህ ነው፡፡ ፍቅር ባእድ ነገር ያልተቀላቀለበት ነው፡፡ ፍቅር ሁለት አላማ የለውም፡፡ ፍቅር ድብቅ አላማ የለውም፡፡ ፍቅር ሌላውን የመጥቀም የማነሳትና የመባረክ ብቸኛ አላማ ነው ያለው፡፡ ፍቅር ውስጡ ራስ ወዳድነት የለበትም፡፡ ፍቅር ከስግብግብነት የፀዳ ነው፡፡ 
ፍቅር በማንም አይታማም
ፍቅር ማንም ነቀፋ አያገኝበትም፡፡ ፍቅር በማንም አይታማም፡፡ ፍቅር በማንም እጅ ከፍንጅ አይያዝም፡፡ ፍቅር በብርሃን ይኖራል፡፡ ፍቅር የሚደብቀው የሚያሳፍር ነገር የለውም፡፡ ፍቅር ግልፅ ነው፡፡
ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤ እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደ ሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል። የዮሐንስ ወንጌል 3፡20-21
ፍቅርን ማንም አይዘውም አያስረውም
ፍቅርን ሊይዘው ሊወስነው የሚችል ነገር የለም፡፡ ፍቅር ነፃ ነው፡፡ ፍቅር በማንም አይታሰርም፡፡ ፍቅርን የራሱን ስለማይፈልግ ማንም አያስፈራራውም፡፡
የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡5
ፍቅርን ማንም አያሰናክለውም
ፍቅር በሰጭው እንጂ በተቀባዩ ላይ ስላልተመሰረተ ፍቅርን ማንም አያሰናክለውም፡፡ ፍቅር የማንንም መልስ ስለማይጠብቅ ማንም አያስደንቀውም፡፡ ፍቅርን ማንም አያሳዝነውም፡፡ ፍቅርን ማንም አያስቆመውም፡፡ ፍቅርን ማንም አያዘገየውም፡፡ ፍቅር ነፃ ነው፡፡
እንግዲህ ከነዚህ ከሦስቱ በወንበዴዎች እጅ ለወደቀው ባልንጀራ የሆነው ማንኛው ይመስልሃል? እርሱም፦ ምሕረት ያደረገለት አለ። ኢየሱስም፦ ሂድ አንተም እንዲሁ አድርግ አለው። የሉቃስ ወንጌል 10፡36-37
ፍቅር አይወድቅም
ፍቅር አላማውን ከማሳካት ወደኋላ አይመለስም፡፡ ፍቅር በፊቱ የሚቆም ማንም የለም፡፡
ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል። ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡4-8
የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው። እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም። ገላትያ 5፡22-23
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፍቅር #መውደድ #መስጠት #መባረክ #ማንሳት #ድፍረት #መልካም #ማካፈል #ሙላት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #ፍርሃት #መታበይ #ራስወዳድነት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment