በፊልድልፍያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ የዳዊት መክፈቻ ያለው፤ የሚከፍት፥ የሚዘጋም የሌለ፤ የሚዘጋ፥ የሚከፍትም የሌለ፤ ቅዱስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል። የዮሐንስ ራእይ 3፡7
የዳዊትንም ቤት መክፈቻ በጫንቃው ላይ አኖራለሁ፤ እርሱም ይከፍታል የሚዘጋም የለም፤ እርሱም ይዘጋል የሚከፍትም የለም። ትንቢተ ኢሳይያስ 22፡22
ኢየሱስ ሞትን አሸንፎ ከመቃብር በመነሳቱ የጌቶች ሁሉ ጌታ የነገስታት ሁሉ ንጉስ ነው፡፡
በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡9-11
ስልጣን በሰማይና በምድር ሁሉ ተሰጥቶታል፡፡
ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ። የማቴዎስ ወንጌል 28፡18
ስለዚህ ኢየሱስ የሚከፍተውን ሊዘጋ የሚችል ምንም ሃይል የለም፡፡ ኢየሱስ የዘጋውን የአለም ሃያል አገር አይከፍተውም፡፡ ኢየሱስ የከፈተውን ደግሞ ሊዘጋ የሚችል ሃይል በሰማይና በምድር የለም፡፡
እርሱ የዘጋውን የሚከፍት እንደሌለ ማወቃችን በተዘጋው ነገር ላይ በከንቱ ጕልበታችንንና ጊዜያችንን እንዳናባክን ይረዳናል፡፡ እርሱ የከፈተውን የሚዘጋ እንደሌለ ማወቃችን ደግሞ በሮች ምንም ያህል የተዘጉ ቢመስሉን ተስፋ እንዳንቆርጥ ያበረታናል፡፡
እርሱ ሁሉን ለራሱ ሊያስገዛ በሚችል አሰራር አለው፡፡
እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር፥ ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3፡21
ስለዚህ ነው በእግዚአብሄር አሰራር እርፍ ልንል የሚገባን፡፡
ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ። መዝሙረ ዳዊት 46፡10
ስለዚህ ነው በእግዚአብሄር አሰራር ሁልጊዜ ደስ ልንሰኝ የሚገባን፡፡
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5፡16
ሥራህን አውቃለሁ፤ እነሆ፥ በአንተ ፊት የተከፈተ በር ሰጥቼአለሁ ማንምም ሊዘጋው አይችልም፤ ኃይልህ ምንም ትንሽ ቢሆን ቃሌን ጠብቀሃልና፥ ስሜንም አልካድህምና። የዮሐንስ ራእይ 3፡8
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #ሃያል #ሁሉንቻይ #የሚዘጋ #የሚከፍት #በር ##ፍፁም #ተመላለስ #ኤልሻዳይ #እምነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment