Popular Posts

Follow by Email

Monday, June 18, 2018

ፍቅር የማይገባውን አያደርግም

ፍቅር . . . የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡5
ፍቅር ስስ ነው፡፡ ፍቅር የሚረዳ ነው፡፡ ፍቅር የመፍትሄ እንጂ የችግር መነሻ ምክንያት መሆን አይፈለግም፡፡  
ወንድሞች ሆይ፥ ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዓት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን። 2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 3፡6
ፍቅር ለህግ ንቁ ነው፡፡ ፍቅር ህግን ያከብራል፡፡ ፍቅር ህግን አይጥስም፡፡ ፍቅር በህግ ለመኖር ይጠነቀቃል፡፡ ፍቅር በስሜታዊነት ጥንቃቄ የጎደለውን እርምጃ አይወስድም፡፡
ወንድሞች ሆይ፥ እንመክራችኋለን፤ ያለ ሥርዓት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤ 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5፡14
ፍቅር አላግባብ አይሄድም፡፡ ፍቅር የሚያደርገው ትክክለኛውን ነገር ነው፡፡ ፍቅር ጨዋ ነው፡፡ ፍቅር የሚያሳፍር ነገር አያደርግም፡፡ ፍቅር የሚያስነቅፍን ነገር አያደርግም፡፡
እኛን ልትመስሉ እንዴት እንደሚገባችሁ ራሳችሁ ታውቃላችሁና፤ በእናንተ ዘንድ ያለ ሥርዓት አልሄድንምና፤ 2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 3፡7
ፍቅር ራሱን ይገዛል፡፡ ፍቅር ጥንቃቄ ያደርጋል፡፡ ፍቅር ስነምግባር አለው፡፡   
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ፍቅር #ወግ #ስርአት #መውደድ #የማይገባውን #የሚገባውን #መንፈስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ትዕግስት #መንፈስቅዱስ #ምስክር #ልብ #መሪ

No comments:

Post a Comment