ያዕቆብም፦
እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፥ ሰውነቴም ድና ቀረች ሲል የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል ብሎ ጠራው። ዘፍጥረት 32፡3
እግዚአብሔርን
አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ። መዝሙር 27፡4
ዓይኖችህ
ንጉሥን በውበቱ ያዩታል፤ እነርሱም በሩቅ ያለች ምድርን ያዩአታል። ኢሳያስ 33፡17
እግዚአብሄርን
እንደማየት የሚያስደስት ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄርን ለማምለክ ስለተሰራን እግዚአብሄርን እንደማየት የሚያረካ ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄርን
እንደማምለክ የሚያሳርፍ ነገር የለም፡፡
እግዚአብሄርን
ስናመልከው አካባቢያችንን እንረሳለን፡፡ እግዚአብሄርን ስናመልከው ከሁኔታችን እንወጣለን፡፡ እግዚአብሄርን
በውበቱ ስናየው እናርፋለን፡፡ እግዚአብሄርን ስናመልከው በጎነቱን እናስታውሳለን፡፡ እግዚአብሄርን እንዳለ ስናየው በሃይሉ እንበረታለን፡፡
እነሆ፥
አሕዛብ በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸው፥ በሚዛንም እንዳለ ትንሽ ትቢያ ተቈጥረዋል፤ እነሆ፥ ደሴቶችን እንደ ቀላል ነገር ያነሣል።
ኢሳይያስ 40፡15
እግዚአብሄርን
እንዳለ ስናየው በጥበቡ እንማረካለን፡፡ በእግዚአብሄርን ስናመልከው በፍቅሩ እንወሰዳለን፡፡ እግዚአብሄርን ስናመልከው በመልካምነቱ
እንረሰርሳለን፡፡ እግዚአብሄርን ስናመልከው ልባችን ከፍ ይላል፡፡ እግዚአብሄርን ስናየው ካለንበት የምድር ስበት ከፍ እንላለን፡፡
በቅዱስ
ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው። 1ኛ ዜና 16፡10
የዘላለሙን
እግዚአብሄርን ስናመልከው የምድር ኑሮዋችን ያጥርብናል፡፡ የዘላለሙን እግዚአብሄርን ስናመልከው ሰማይን እናያለን፡፡ መጀመሪያና መጨረሻ
የሆነውን እግዚአብሄርን ስናመልከው ዘላለምን እንመለከታለን፡፡
ያለውና
የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።ራእይ 1፡8
እግዚአብሄርን
ስናመልከው መጀመሪያና መጨረሻ በሆነው በእግዚአብሄር እንወሰዳለን፡፡ ታላቁን እግዚአብሄርን ስናመልከው ያለንበት ፈታኝ ሁኔታ ያንስብናል፡፡
መኖሪያችን እግዚአብሄርን ታላቅነት ስናይ የኑሮ ፍርሃት ከህይወታችን ይሞታል፡፡
መኖሪያህ
የዘላለም አምላክ ነው፥ የዘላለምም ክንዶች ከአንተ በታች ናቸው፤ ዘዳግም 33:27
ማስተዋሉ
የማይመረመረውን እግዚአብሄርን ስናመልከው የህይወት ጥያቄያችንን ፈልገን እናጣዋለን፡፡ ባለጠጋውን እግዚአብሄርን ስናመልከው በባለጠግነቱ
እንመካለን፡፡
የምድረ
በዳ አራዊት ሁሉ በሺህ ተራራዎች ያሉ እንስሶችም የእኔ ናቸውና። መዝሙር 50፡10
ሃያሉን
እግዚአብሄርን ስበናመልከው የራሳችንን ድካም እንረዳለን፡፡ ማስተዋሉ የማይመረመረውን እግዚአብሄርን ስናምለከው ያለንን ውስንነት
እንረሳለን፡፡ ሁሉን ማድርግ የሚችለውን እግዚአብሄርን በውበቱ ስናየው መንገዳችን ይቀልልናል፡፡
ሁሉን
ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ፥ አሳብህም ይከለከል ዘንድ ከቶ እንደማይቻል አወቅሁ። ኢዮብ 42፡2
የምድር
መሰረቶች የእርሱ የሆኑትን እግዚአብሄርን በክብሩ ስናየው በአባታችን ደስ እንሰኛለን፡፡
ከሕዝቡ
መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፤
የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አደረገ። 1ኛ ሳሙኤል 2፡8
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #አምልኮ #መገዛት #ቃል #ደስታ #እርካታ #እህል #መመልከት #ማየት
#ተመልክተን #መቃጠል #መቀጣጠል #ክብር #አገልግሎት #መዋረድ #መርካት #ፀጋ #እውቀት #ኢየሱስንተመልክተን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #እምነት #ታላቅነት #ማገልገል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment