Popular Posts

Friday, June 8, 2018

ለሰይጣን ሽንገላ ፍቱን መድሃኒቱ

ሰይጣን በትእቢት ምክንያት ከመውደቁ በፊት የእግዚአብሄር አገልጋይ ነበር፡፡ ሰይጣን የእግዚአብሄርን ቦታ ፈልጎ ከመዋረዱ በፊት በእግዚአብሄር ጥበብ ይኖር ነበር፡፡ ሰይጣን በሃጢያት ምክንያት ሲወድቅ ነው ጥበብህን አረከስህ የተባለው፡፡
በውበትህ ምክንያት ልብህ ኰርቶአል፤ ከክብርህ የተነሣ ጥበብህን አረከስህ፤ በምድር ላይ ጣልሁህ ያዩህም ዘንድ በነገሥታት ፊት ሰጠሁህ። ሕዝቅኤል 28፡17
ሰይጣን የረከሰ ጥበብ ይሁን እንጂ አሁንም ጥበብ አለው፡፡ ሰይጣን ይዋሻል፡፡ ሰይጣን ሰዎችን ያሳምናል፡፡ ሰይጣን ሰዎችን ያታልላል፡፡ ሰይጣን በረከሰው ጥበብ ተጠቅሞ ሰዎችን ያስታል፡፡ ሰይጣን ጥበቡን ተጠቅሞ ሰዎችን በእግዚአብሄር ላይ ያሳምፃል፡፡ ሰይጣን ጥበቡን ተጠቅሞ የሰዎችን ህይወት ያጠፋል ያበላሻል፡፡
ሰይጣን ሰዎችን በማታለል ይሰርቃል ያርዳል ያጠፋል፡፡   
ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። ዮሃንስ 10፡10
ሰይጣን ይዋሻል፡፡ ሰይጣን ሰዎችን ያስታል፡፡ ሰይጣን ሄዋንን አስቶዋታል፡፡ ሰይጣን በእግዚአብሄር ጥበብ በቀጣይነት የማይኖረውን ማንኛውንም ሰው ሊያስት ይችላል፡፡
እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና። ዮሃንስ 8፡44
ሰይጣን አያታልለንም ብለን በከንቱ ብንፎክር ከሰይጣን ማታለል አናመልጥም፡፡ ሰይጣን የራሱ የማታለል ሃይለ አለው፡፡ ሰይጣን ምንም አያመጣም ብለን ብንኩራራ ራሳችን ምንም አናመጣም፡፡
የረከሰ ጥበብ ይሁን እንጂ ሰይጣን የራሱ ጥበብ ስላለው ካለ እግዚአብሄር ጥበብ በስተቀር ከሰይጣን ማታለል ማምለጥ አንችልም፡፡ በሰይጣን ላለመሳት ከፈለግን የእግዚአብሄር ጥበብ ያስፈልገናል፡፡ የሰይጣንን ሽንገላ የምንቃወምበት የእግዚአብሄርን ጥበብ ማንሳይ አለብን፡፡ ካለ እግዚአብሄር ጥበብ የሰይጣንን ሽንገላ መቃወም አንችልም፡፡  
ካለ እግዚአብሄር ጥበብ የሰይጣንን ሽንገላ የምንቃወም ከመሰለን በራሱ በሰይጣን ተታልለናል ማለት ነው፡፡ በሰይጣን ላለመበለጥ የሰይጣንን ማታለል የሚበልጥ ጥበብ ያስፈልገናል፡፡ የምንበረታው በራሳችን ሃይል ሳይሆን በጌታ ሃይል ብቻ ነው፡፡
በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ። የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ። ኤፌሶን 6፡10-11
ከእግዚአብሄር ብቻ በምናገኘው ዘርፈ ብዙ ጥበብ በመታገዝ ብቻ ነው የሰይጣንን ሽንገላ እያለ በእኛ ላይ ምንም ሃይል እንዳይኖረው ማድረግ የምንችለው፡፡ በአለቆችና ስልጣናት ላይ በሃይል የምንገለጠው በእግዚአብሄር ጥበብ ስንንቀሳቀስ ብቻ ነው፡፡
ብዙ ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት ትታወቅ ዘንድ፤ ኤፌሶን 3፡10
በእግዚአብሄር ቃል ጥበብ ስንኖር ግን ኢየሱስ እንዳለው ሰይጣን በእኔ ላይ አንዳች የለውም ማለት እንችላለን፡፡
ከእንግዲህ ወዲህ ከእናንተ ጋር ብዙ አልናገርም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ይመጣልና፤ በእኔ ላይም አንዳች የለውም፤ ዮሃንስ 14፡30
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ጥበብ #ማስተዋል #ሽንገላ #አለቆች #ስልጣናት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰይጣን #ዲያብሎስ #እምነት #ፈተና #ፀሎት #ጌታ #የእግዚአብሄርቃል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment