Popular Posts

Saturday, June 2, 2018

ሰዎች ሁሉ የሚያውቁትና የሚያነቡት መልእክታችን

እንደ ገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ እንደ ሌሎች የማመስገኛ መልእክት ወደ እናንተ ወይስ ከእናንተ ያስፈልገን ይሆንን? ሰዎች ሁሉ የሚያውቁትና የሚያነቡት በልባችን የተጻፈ መልእክታችን እናንተ ናችሁ። እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፥ ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 3፡1-3
እንደ ቃል አገልጋይ የአገልግሎት ስራችን የሚመዘነው በውጤት ነው፡፡ የቃል አገልጋይነት ሊመዘን የማይችል ረቂቅ ሚስጥር አይደለም፡፡ የቃል አገልጋይነት ፍሬ ሊደረስበት የማይችል ስውር ሚስጥር አይደለም፡፡  
የአገልግሎት ውጤታችን ደግሞ የሚለካው በአገለገልነው ሰው ብዛት አይደለም፡፡ የአገልጋይ የአገልግሎት ስኬታማነት የሚለካው በቤተክርስትያኑ ህንፃ ማማር አይደለም፡፡ የአገልግሎት ስምረት የሚለካው ቤተክርስትያን ባከማቸችው የገንዘብ መጠን አይደለም፡፡ የቤተክርስትያን ስኬት የሚለካው በቤተክርስትያን ዝና መጠን አይደለም፡፡  
የሚገለገል ሰው ሲበዛ ተፅእኖዋችን ይባዛል ነገር ግን የሚያስፈልግው ነገር ተፅእኖ ነው፡፡ የሰው መብዛት ብቻ ስለተፅእኖ ሊናገር አይችልም፡፡ ሁላችንም የሚያምር ነገር እንፈልጋለን፡፡ የምንሰበሰብበት የቤተክርስትያን ህንፃ ቢያምርና ምቹ ቢሆን መልካም ነው፡፡ ነገር ግን የምንሰበሰብበት አላማ ግቡን ካልመታ ከንቱ ነው፡፡ ለአገልግሎት ገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን የገንዘብ መኖር የአገልግሎታችንን ግብ መምታት አያሳይም፡፡ ገንዘቡን ለአገልግሎት አላማ ካልዋለ ከንቱ ነው፡፡
የአገልግሎት አላማ የእግዚአብሄርን ቃል በሰው ውስጥ መቅረፅ ነው፡፡ የአገልግሎት አላማ ሰዎች የእግዚአብሄርን ቃል እንዲረዱ መስበነክና ማስተማር ነው፡፡ የአገልግሎት አላማ ሰዎች የእግዚአብሄርን ቃል እንዲያደርጉ የሚያስችላቸውን እውቀት መስጠት ነው፡፡ የአገልግሎት አላማ የሰዎች ህይወትይ በእግዚአብሄር ቃል መለወጡ ነው፡፡ የአገልግሎት አላማ ሰዎች በእግዚአብሄር ቃል ሲኖሩ ማየት ነው፡፡
የአገልግሎት አላማ ሰዎች ሁሉ በግልፅ የሚያነቡትን መንፈሳዊ ህይወትን በሰዎች ውስጥ ማሳደግ ነው፡፡ የአገልግሎት አላማ ሰዎች ሁሉ የሚያነቡትን በቃሉ የተነካን ልብ መፍጠር ነው፡፡ የአገልግሎት አላማ ሰዎች ሁሉ ሊያዪ የሚችሉትን በልብ ላይ የተፃፈ የእግዚአብሄርን ቃል አሻራ መተው ነው፡፡
ስለአገልግሎታችን መመስከር ያለበት የተለወጠ ሰው ነው፡፡ ስለእኛ አገልግሎት መልእክት ማስተላለፍ ያለበት በስብከታችን እና በትምህርታችን የተለወጡ ሰዎች የህይወት እርምጃ ነው፡፡ ስለአገልግሎታችን መናገር ያለበት የሰዎች ህይወት ለጌታ መሰጠትና ንፅህና ነው፡፡ ስለአገልግሎታችን መመስከር ያለበት በጌታ ኢየሱስ የተነካ የሰዎች ህይወት ነው፡፡
የእኛ የምስጋና ደብዳቤ በእጅ የተፃፈ ደብዳቤ ሳይሆን በእግዚአብሄር ቃል የተቀረፀ የሰዎች ህይወት ነው፡፡ የእኛ የምስጋና ደብዳቤ በእግዚአብሄር ቃል የተለወጠ የሰዎች መንፈሳዊ ህይወት ነው፡፡ የእኛ የምስጋና ደብዳቤ ሰዎች ሁሉ ሊያነቡት የሚችሉት የተለወጡ ሰዎች የክርስትና ህይወት ነው፡፡  
እንደ ገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ እንደ ሌሎች የማመስገኛ መልእክት ወደ እናንተ ወይስ ከእናንተ ያስፈልገን ይሆንን? ሰዎች ሁሉ የሚያውቁትና የሚያነቡት በልባችን የተጻፈ መልእክታችን እናንተ ናችሁ። እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፥ ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 3፡1-3
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #መንፈስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አገልጋይ #መንፈስቅዱስ #ምስክር #ልብ #መሪ

No comments:

Post a Comment