ሰዎችን ተጠቅሞ የሚያሸብረው ሰይጣን ነው፡፡ ሰይጣን
የተሸነፈ ጠላት ነው፡፡ ሰይጣን የተፈረደበት ተስፋ የሌለው ጠላት ነው፡፡
ስለ ፍርድም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ስለ ተፈረደበት
ነው። የዮሐንስ ወንጌል
16፡11
ሰይጣን ፍቅርን አያውቅም፡፡ ሰይጣን ምህረት አይገባውም፡፡
ሰይጣን በፍቅርና በሰላም ምንም ነገር ማድረግ ስላይችል የሚችለው አንድ ነገር ውሸትን በመዋሸት ፍርሃትን በሰዎች ውስጥ በመጨመር
ከመንገዳቸው ማስቆም ነው፡፡ ሰይጣን ውሸትን በማዛመት ማስፈራራት
ስራው ነው፡፡
እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና። የዮሐንስ ወንጌል 8፡44
ሰይጣን የሰዎችን ጉስቁልና እንጂ እድገት አይፈልግም፡፡
ሰይጣን የሰዎችን መቆም እንጂ መራመድ እና እድገት አይፈልግም፡፡ ስለዚህ ሰይጣን ራስ ወዳድ ምኞታቸውን ብቻ የሚከተሉ ፣ ለሌላው
ምንም ፍቅር እና አክብሮት የሌላቸው ሰዎችን ለማስፈራሪያነት እንደመሳሪያ
ይጠቀማል፡፡
እግዚአብሄር ሰውን ሲፈጥረ ፈቃድ ሰጥቶታል፡፡
እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ሲከፈት የሚከፈት ሲዘጋ የሚዘጋ የራሱ ፈቃድ የሌለው ሬዲዮ ወይም ቴሌቪዥን አድርጎ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር
ሰውን የፈጠረው በሙሉ ፈቃድ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚገዛው በፍቅር እና በፈቃደኝት ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰዎች እንዲገዙለት የሚፈልገው
በፍቅርና በፈቃደኝነት ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር ፍቅር ነው ሰውን ማሸነፍ የሚፈልገው በማስፈራራት ሳይሆን በፍቅር ነው፡፡
የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3፡1
በፍርሃት ሊገዛ የሚፈልውገው ሰይጣን ብቻ ነው፡፡
ሰይጣን የሚሰራው በጥላቻ ነው፡፡ ሰው ውስጥ ጥላቻን ካላስገባ በስተቀር ሰይጣን መስራት አይችልም፡፡ ሰው ውስጥ ጥላቻን ካስገባ
ደግሞ የማይሰራው ክፋት የለም፡፡ ሰው ውስጥ ጥላቻ ካስገባ ሰውን ያስገድላል፡፡
እኛ
ወንድሞችን የምንወድ ስለ ሆንን ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገርን እናውቃለን፤ ወንድሙን የማይወድ በሞት ይኖራል። ወንድሙን የሚጠላ
ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3፡14-15
ሰይጣን ደግሞ ራስ ወዳድ ሰዎችን ለማረድ ለማጥፋትና
ለመስረቅ አላማው ይጠቀማል፡፡
ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።የዮሐንስ ወንጌል 10፡10
እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም
ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር
ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና። የዮሐንስ ወንጌል 8፡44
የአሸባሪነት አላማ ደግሞ ሰውን ከጉዞው ማስቆም
ነው፡፡ ሰውን ዝም ካላሰኘና ከአላማው ካላስቆመው ፍርሃት አላማው ይከሽፋል፡፡ ሰውን ከመንገዱ ከላስቆመው አሸባሪነት ግቡን አይመታም፡፡
እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ። ወደ ዕብራውያን 2፡14-15
ሰይጣን ባገኘው አጋጣሚ መታወስ ይፈልጋል፡፡ ሰይጣን
ባገኘው አጋጣሚ የፍርሃት ዜናውን ማሰራጨት ይፈልጋል፡፡ የሰይጣን አላማ በፍርሃት ሽባ ማድረግ ነው፡፡ የሰይጣነ አላማ በውስጣችን
ያለውን እምቅ ጉልበት እንዳንጠቀም አሳስሮ ማስቀመጥ ነው፡፡
ሰይጣን አያስቆመንም፡፡ በፍቅር ፍርሃትን አሽቀንጥረን
እንጥላለን፡፡ በፍቅር እንሄዳለን፡፡ በፍቅር እንወጣለን እንገባለን፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች
ሼር
share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #ፍትህ #ፍርድ #ዲያቢሎስ #ሰይጣን
#ዲሞክራሲ #ሊሰርቅ #ሊያርድ #ሊያጠፋ #ፍርሃት #የውሸት አባት #ኢትዮጲያ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ወንጌል #ጥላቻ #ፍቅር #ፈቃድ #መሪ
No comments:
Post a Comment