Popular Posts

Follow by Email

Sunday, June 10, 2018

የጌታ መንፈስ አብሮን እንዲሆንና በሃይል እንዲሰራ የሚያደርጉ 5 ነገሮች

የእግዚአብሄር መንፈስ መገኘት ለማንኛውም ጥያቄያችን መልስ ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ ሲገኝ በህይወታችን ሙሉ ነፃነትን እንለማመዳለን፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ ሲገኝ በህይወታችን የማይቻል ነገር አይኖርም፡፡  
ጌታ ግን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ። 2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 317
እኛ የምናደርጋቸው የእግዚአብሄርን መንፈስ የሚያሳዝኑት ነገሮች አሉ፡፡ እኛ የምናደርጋቸው የእግዚአብሄርን መንፈስ የሚያስደስቱት ነገሮች አሉ፡፡
ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡30
የእግዚአብሄርን መንፈስ የሚስቡ ባህሪዎች አሉ፡፡ የእግዚአብሄርን መንፈስ የሚገፉ ባህሪዎችም አሉ፡፡
የልብ ንፅህና
የእግዚአብሄር መንፈስ በሃይል እንዲገኝና ከእኛ ጋር አብሮ እንዲሰራ ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ የልባችን ንፅህና ነው፡፡ እግዚአብሄር ቅዱስና ንፁህ ስለሆነ ንፁህ ነገር ይስበዋል፡፡
ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፥ እግዚአብሔርን ያዩታልና። የማቴዎስ ወንጌል 5፡8
ትህትና
እግዚእብሄር ትእቢተኛን ይቃወማል ለትሁታንም ፀጋን ይሰጣል፡፡ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5፡5
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው? ትንቢተ ኢሳይያስ 66፡1-2
እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ።
እግዚአብሄርን መፍራት
ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ይወጣል? በቅድስናውስ ስፍራ ማን ይቆማል? እጆቹ የነጹ፥ ልቡም ንጹሕ የሆነ፥ ነፍሱን ለከንቱ ያላነሣ፥ ለባልንጀራውም በሽንገላ ያልማለ። እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ በረከትን ከመድኃኒቱ አምላክም ምሕረትን ይቀበላል። መዝሙረ ዳዊት 24፡3-5
ሕይወትን ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ ሰው፥ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤ ከክፉ ፈቀቅ ይበል፥ መልካምንም ያድርግ፥ ሰላምን ይሻ ይከተለውም፤ የጌታ ዓይኖች ወደ ጻድቃን ናቸውና፥ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል፥ የጌታ ፊት ግን ክፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፡10-12
ምስጋና
በሆነው ባልሆነው የማያጉረመርም ሰው የእግዚአብሄርን መንፈስ አብሮይት ሊሀና ሊሰራ አይችልም፡፡ እግዚአብሄን በነገር ሁሉ የሚያመሰግን ሰው ግን የእግዚአብሄር መንፈስ አብሮት ይሰራል በሚያልፍበት ነገር ሁሉ ውስጥ አብሮት ይሆናል ያሳልፈዋል፡፡
አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ። በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም። ትንቢተ ኢሳይያስ 43፡2-3
ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ። መዝሙረ ዳዊት 50፡23
መፈለግ
ሙሴም እግዚአብሔርን፦ እነሆ አንተ፦ ይህን ሕዝብ አውጣ ትለኛለህ፤ ከእኔም ጋር የምትልከውን አላስታወቅኸኝም። አንተም፦ በስምህ አወቅሁህ፥ ደግሞም በእኔ ፊት ሞገስን አገኘህ አልኸኝ። አሁንም በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ፥ አውቅህ ዘንድ በፊትህም ሞገስን አገኝ ዘንድ መንገድህን እባክህ አሳየኝ፤ ይህም ሕዝብ ሕዝብህ እንደ ሆነ ተመልከት አለው። እግዚአብሔርም፦ እኔ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፥ አሳርፍህማለሁ አለው። እርሱም፦ አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህስ፥ ከዚህ አታውጣን። ኦሪት ዘጸአት 33፡12-15
እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ። ከእናንተም ዘንድ እገኛለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ምርኮአችሁንም እመልሳለሁ፥ ትንቢተ ኤርምያስ 29፡13-14
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #መገኘት #ህልውና #ቃል #ህልዎት #የጌታመንፈስ #አብሮነት #ክብር #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ምስክርነት #አማርኛ #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ነፃነት #ሞገስ #እረፍት #እርካታ #አርነት #ንፅህና #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #ፌስቡክ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment