እናንተ
የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም። መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል። መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ። ማቴዎስ 5፡14-16
ለእይታ
ብርሃን በጣም እስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ሰው አይን ስላለው ብቻ አያይም፡፡
አይን ያለው ሰው ለማየት ብርሃን ያስፈልገዋል፡፡ ሰው ካለብርሃን ምንም ነገር ማየት አይችልም፡፡ ሰው ቀለምን እንዲለይ ብርሃን
ያስፈልገዋል፡፡ ሰው እንዲያይ ብርሃን ያስፈልገዋል፡፡
ካለብርሃን
ሰው ማየት ስለማይችል የብርሃንነት ሃላፊነት በጣም ወሳኝ ሃላፊነት ነው፡፡
ኢየሱስ
እናንተ የአለም ብርሃን ናችሁ ሲል በቃላችንና በኑሮዋችን ሰው እንዲያይ ማድረግ እንደምንችል እየነገረን ነው፡፡ ኢየሱስ እናንተ
የአለም ብርሃን ናችሁ ሲል ብርሃን ያለበትን ወሳኝ ሃላፊነት እያስታወሰን ነው፡፡
እኛ
ካላሳየነው በጨለማ የሚሄደው ሰው ነገሮችን ማየት አይችልም፡፡ እኛ ብርሃን ሆነን ካላሳየነው በጨለማ ያለ ሰው የእግዚአብሄርን መንግስት
ሊያይ አይችልም፡፡ እኛ ብርሃን ሆነን እግዚአብሄርን ካላሳየነው በጨለማ ያለው ህዝብ እግዚአብሄርን ማየት አይችልም፡፡ እኛ ብርሃን
ሆነን ካላሳየነው በጨለማ ያለ ህዝብ የዘላለምን ህይወት ማየት አይችልም፡፡ እኛ ብርሃን ሆነን ካላሳየነው በመታለል የሚኖረው ህዝብ
እውነትን ማየት አይችልም፡፡ እኛ ብርሃን ሆነን ካላሳየነው በሰይጣን ግዛት ውስጥ በጭቆና የሚኖረው ህዝብ የእግዚአብሄርን ፍቅርና
ይቅርታ ማየት አይችልም፡፡
ደግሞም
ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው። የዮሐንስ
ወንጌል 8፡12
ኢየሱስ
የአለም ብርሃን ሆኖ በምድር ላይ ተመላልሷል፡፡ ኢየሱስ ብርሃን ሆኖ እግዚአብሄርን አሳይቶናል፡፡ ኢየሱስ ብርሃን ሆኖ የዘላለም
ህይወትን አሳይቶናል፡፡ ኢየሱስ ብርሃን ሆኖ የነበርንበትን የውድቀት ህይወት አሳይቶናል፡፡ ኢየሱስ ብርሃን ሆኖ የእግዚአብሄርን
የመዳኛ መንገድ አሳይቶናል፡፡ ኢየሱስ ብርሃን ሆኖ ዋጋ የሚሰጠውንና የማይሰጠውን ነገር ለይቶ አሳይቶናል፡፡ ኢየሱስ ብርሃን ሆኖ
የእግዚአብሄርን መንግስት አሳይቶናል፡፡ ኢየሱስ ብርሃን ሆኖ ፍጸፃሜያችንን አሳይቶናል፡፡
በነቢዩም
በኢሳይያስ፦ የዛብሎን ምድርና የንፍታሌም ምድር፥ የባሕር መንገድ፥ በዮርዳኖስ ማዶ፥ የአሕዛብ ገሊላ፤ በጨለማ የተቀመጠው ሕዝብ
ታላቅ ብርሃን አየ፥ በሞት አገርና ጥላ ለተቀመጡትም ብርሃን ወጣላቸው የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ። የማቴዎስ ወንጌል 4፡14-16
አሁንም
እኛ ብርሃን ሆነን እግዚአብሄርን መፍራትን ለሌሎች እናሳያለን፡፡ እግዚአብሄርን በመፍራት ሌሎች እግዚአብሄርን እንዲፈሩ በኑሮዋችን
እናስፈራራለን፡፡ እኛ ብርሃን በመሆን ሰዎች የሚኖሩትን የሃጢያት ህይወት እንገልጣለን፡፡ እኛ ብርሃን በመሆን ክርስትና እንደሚቻል
ለሰዎች መገለጥን እንሰጣለን፡፡
ብርሃንም
ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው። ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን
ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤ ዮሃንስ 3፡19-20
እኛ
ብርሃን በመሆን ሰዎች እግዚአብሄርን የሚያገኙበትን መንገድ እናሳያለን፡፡ እኛ ብርሃን በመሆን በሃጢያት ምክኒያት ሰዎች ያሉበትን
ውድቀት እናሳያለን፡፡ እኛ ብርሃን በመሆን ሰዎች የተዋረደውን ከከበረው እንዲለዩ እናሳያለን፡፡ እኛ ብርሃን በመሆን ሰዎች የዘላለም
ህይወትን እንዲያዩ እናደርጋሃል፡፡ እኛ ብርሃን በመሆን ሰዎች የእግዚአብሄርን መንግስት አሰራር እንዲለዩ እናደርጋለን፡፡ እኛ ብርሃን
በመሆን ሰዎች የእግዚአብሄርን ፍቅር እንዲያዩት እናደርጋለን፡፡ እኛ ብርሃን በመሆን የእግዚአብሄርን ሃይል ብርታት እናሳያለን፡፡
እኛ ብርሃን በመሆን የሚያድነውን የእግዚአብሄርን ፀጋ እናሳያለን፡፡
ሰዎችን
ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ ወደ ቲቶ 2፡11
እናንተ
የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም። መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ
ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል። መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ
በሰው ፊት ይብራ። ማቴዎስ 5፡14-16
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #ልጅነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #ዝራ #የምድርጨው #የአለምብርሃን #ጨለማ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ምስክርነት
#አማርኛ #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ጥሪ #ክህንነት #ስራ #መልክተኛ #አምባሳደር #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #ፌስቡክ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment