ጊዜው የአለም የእግር ኳስ ዋንጫ ጫወታ ጊዜ ነው፡፡
ግብ የሚለውን ነገር ለመረዳት እንደዚህ ጊዜ ምቹ ጊዜ አይገኝም፡፡ ለእግር ኳስ ጫወታ ግብ በጣም ማስፈለግ ብቻ አይደለም ለማሸነፍ
ግብ ወሳኝ ነው፡፡
32 የአለም የገራት ክለቦች ለአለም ዋንጫ ፍፃሜ
ውድድር ለመጫወት በሩሲያ ተሰብስበዋል፡፡ ጫወታው ከመጀመሩ በፊት ሁሉም የማሸነፍ 100% እድል አላቸው፡፡
ጫወታ ከመጀመሩ በፊት ሁሉም ጥሩ ክለቦች ናቸው፡፡
ጫወታ ሲጀመር ግን አንዱ ከአንዱ እየተለየ አንዱ ከአንዱ እየራቀ አንዱ አንዱን ጥሎት ይሄዳል፡፡
እነዚህ ተመሳሳይ የሚመስሉት ክለቦችን የሚለያቸው
አንድ ነገር ብቻ ነው፡፡ እነዚህን ለመለየት የሚያስቸግሩ ክለቦችን የሚለያቸው ግብ ማስቆጠር ነው፡፡
ግብ የሚያስቆጥር ይለያል፡፡ ግብ የሚያስቆጥር
ያሸንፋል፡፡ እንዴት ግብ እንደሚያስቆጥር የሚያውቅ ውጤያማ ይሆናል፡፡ እንዴት ግብ ማስቆጠር እንዳለበት የማያውቅ ደግሞ እየተለየ
እየራቀ ይሄዳል፡፡
እግዚአብሄር የሰውን ፊት አይቶ አያዳላም፡፡ ለእያንዳንዳችን
ለማሸነፍ እና ለፍሬያማነት እኩል እድልን ሰጥቶና፡፡
በህይወታችንም አንዳችንን ከአንዳችን የሚለየን
ግብ ነው፡፡ አላማውን የሚያውቅ አላማውን ለማስፈፀም ተግቶ የሚሰራ ሰው አለ፡፡ ካለ አላማ እንዳመጣለት የሚኖር ሰው ደግሞ አለ፡፡
የእግዚአብሄርን አላማ ለማገኘት የሚተጋ ሰው አለ፡፡ ለእግዚአብሄር አላማ ቸልተኛ የሆነ የመሰለውን የሚያደርግ ሰው ደግሞ አለ፡፡
እንደአለም ዋንጫ የእግር ኳስ ጫወታ የህይወት
ግብ ማስቆጠር ግልፅ ብሎ ላይታይ ይቻላል፡፡ ነገር ግን የህይወት ግብ ማስቆጠር ከአለም ዋንጫ ግብ ማስቆጠር ይልቅ እጅግ የከበረ
ነው፡፡
የአለም ዋንጫ ግብን ማስቆጠር በሰዎች ተቀባይነት
ያሰጠናል፡፡ የህይወትን አላማ ግብ መምታት በእግዚአብሄ ዘንድ መልካመ ባሪያ ያስብለናል፡፡
ጌታውም፦ መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው። የማቴዎስ ወንጌል 25፡21
የአለም ዋንጫ ግብ ማስቆጠር የጊዜያዊውን ዋንጫ
የሚያሰጠን ይሆናል፡፡ የህይወት ግብ ማስቆጠር ግን የማይጠፋውን የህይወት አክሊል ያሰጣል፡፡
የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ
ነው፥ እኛ ግን የማይጠፋውን። ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፥ ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም፤
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡25-26
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #አክሊል
#ሽልማት #ትንሳኤ
#ሰማይ #የማይጠፋአከሊል
#አማርኛ #ስብከት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#የአለምዋንጫ #እግርኳስ #ጫወታ #ብፅእና #አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment