እንዳይፈረድባችሁ
አትፍረዱ፤ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፥ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል። በወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፥ በዓይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም? ወይም ወንድምህን፦ ከዓይንህ ጉድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ እንዴትስ ትለዋለህ? እነሆም፥ በዓይንህ ምሰሶ አለ። አንተ ግብዝ፥ አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ፥ ከዚያም በኋላ ከወንድምህ ዓይን ጉድፉን ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ። ማቴዎስ 7፡1-5
አትፍረዱ ማለት አታመዛዝኑ ማለት አይደለም፡፡
አትፈረዱ ማለት ሳትለዩ ሳትፈትኑ ሁሉን ተቀበሉ ማለት አይደለም፡፡
አትፍረዱ ማለት በክፉ ሃሳብ አትፍረዱ ማለት ነው፡፡
አትፍረዱ ማለት በጥላቻ ፣ በቅናት ወይም በትእቢት ተነሳሰታቸሁ አትፍረዱ ማለት
ነው፡፡ የምትጠሉትን ሰው በትክክል ልትፈርዱበት አትችሉም፡፡ በምትጠሉት ሰው ላየ የምትሰጡት የፍርድ አስተያየታችሁ ስለሚበላሽ ትክክለኛ
ፍርድን መፍረድ አትችሉም፡፡ የምትጠሉትን ሰው በትክክለኛ መነፅር ማየት አትችሉም፡፡ በቅናት መነፅር የምታዩትን ሰው ደግሞ በትክክለ
ልታዩት አትችሉም፡፡ ዝቅ አድርጋችሁ በትእቢት የምታዩት ሰው ላይ የምትፈርዱት ፍርድ ቅን ፍርድ የማይሆነው እይታችሁ ስለደበዘዘ
በቀጥታ ማየት ስለማትችሉ ነው፡፡ በፉክክርና በትእቢት የምታዩት ሰው ላይ የሚኖራችሁ አስተያየት እና ፍርድ የተዛበ ነው፡፡
ወንድሞቼ ሆይ፥ በክብር ጌታ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን እምነት ለሰው
ፊት በማድላት አትያዙ። የወርቅ ቀለበት ያደረገና የጌጥ ልብስ የለበሰ ሰው ወደ ጉባኤአችሁ ቢገባ፥ እድፍ ልብስም የለበሰ ድሀ ሰው
ደግሞ ቢገባ፥ የጌጥ ልብስም የለበሰውን ተመልክታችሁ፦ አንተስ በዚህ በመልካም ስፍራ ተቀመጥ ብትሉት፥ ድሀውንም፦ አንተስ ወደዚያ
ቁም ወይም ከእግሬ መረገጫ በታች ተቀመጥ ብትሉት፥ ራሳችሁን መለያየታችሁ አይደለምን? ክፉ አሳብ ያላቸውም ዳኞች መሆናችሁ አይደለምን?
ያዕቆብ 2፡1-4
አትፍረዱ ማለት የምትፈርዱበት ሚዛን ይስተካከል ማለት ነው፡፡
አትፍረዱ ማለት የምትፈርዱበት ሚዛን ካልተስተካከለ በስተቀር የምትፈርዱት ፍርድ
ትክክል አይሆንም ማት ነው፡፡ አትፍረዱ ማለት ከራሳችሁ ጥቅም አንፃር ነገሮችን አትመልከቱ ማለት ነው፡፡ አትፍረዱ ማለት ከስጋዊ
ፍላጎት አንፃር አትፍረዱ ማለት ነው፡፡ አትፍረዱ ማለት ከመንፈስ ሳይሆን ከክፉ የስጋ ፍላጎት አንፃር አትፍረዱ ማት ነው፡፡
እናንተ
ሥጋዊ ፍርድን ትፈርዳላችሁ፤ እኔ በአንድ ሰው ስንኳ አልፈርድም። ዮሃንስ 8፡15
አትፍረዱ ማለት በትክክለኛ እይታ ብቻ ፍረዱ ማለት ነው፡፡
አትፍረዱ ማለት በአድልዎ አትፍረዱ ማለት ነው፡፡
አትፍረዱ ማለት በመልክ አትፍረዱ ማለት ነው፡፡ አትድፍረዱ ማለት አይናችሁ እንዳየ አትፍረዱ ማለት ነው፡፡ አትፍረዱ ማለት እግዚአብሄር
እንደሚያይ ፍረዱ ማለት ነው፡፡
ቅን
ፍርድ ፍረዱ እንጂ በመልክ አትፍረዱ። ዮሃንስ 7፡24
አትፍረዱ
ማለት ከእግዚአብሄር ቃል መመዘኛ ውጭ አትፍረዱ ማለት እንጂ በእግዚአብሄር ቃል አትፍረዱ ማለት አይደለም፡፡ አትፍረዱ ማለት በፅድቅ
ፍረዱ ማለት እንጂ አትመዝኑ አትፈትሹ አትፍረዱ ማለት አይደለም፡፡
ዓይኑም
እንደምታይ አይፈርድም፥ ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንም፤ ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፥ ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል፤
ኢሳያስ 11፡3-4
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #ህይወት #የሚፈርድ #የሚያማ #ወንጌል #መውደድ #ፍቅር #የህይወትምስክርነት #መታዘዝ #ማገልገል #መውደድ #እውነት #ትህትና #ትንሳኤ #ህይወት #ወንጌል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment